Tender Detail

Tender Details

  • Company ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
  • Address ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 212 5402
  • Website
  • Deadline01 May 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-05-01 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተዘረዘሩትን የምግብ እሀል ምርቶች በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን


የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተዘረዘሩትን የምግብ እሀል ምርቶች በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ/ቁ

 

የምርት ዓይነት

 

መለኪያ

 

ብዛት

 

የሚሽጥበት ቦታ

 

ሎት

 

የጨረታ ማስከበርያ

1

 

ለምግብነት የሚያገለገል በቆሎ

በኩንታል

 

4834

 

አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሸን ሃዋሳ

1

 

450,000

 

2

 

ለምግብነት የሚያገለገል ጤፍ

በኩንታል

 

410

 

አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሸን ሃዋሳ

2

 

150,000

 

3

 

ለምግብነት የሚያገለገል ገብስ

በኩንታል

 

219

 

አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሸን ሃዋሳ

3

 

32,850

 

 

1.     ከላይ የተዘረዘረ ምርት መግዛት የሚችሉ።

2.     የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በየለቱ በተቀመጠው መሠረት በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURANTEE ወይም unconditional Bank Guarantee/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3.     ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አደጋ ሥጋት እና የድጋፍ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ግዢ ፋይናንስ ን/አ/ዳሬክቶሬት በመከፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

4.     የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ (bid bond security) ፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) ከተጨማሪ አንድ ኮፒ ሰነድ ጋር በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድረሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግዢ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.     ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰኣት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ይከፈታል፤ ይሁንና የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም።

6.     ሻጩ መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7.     የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይከናወናል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462124639 መደወል ይችላሉ።

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

Save Tender