በየካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የኮተቤ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የኮተቤ ጤና ጣቢያ
2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ጤና ጣቢያ የጨረታ ቁጥር 002/2018 ዓ/ም
ሎት 1. የደንብ ልብስ cpo ብር (6,000)
ሎት 2. የጽዳት እቃዎች cpo ብር (6,000)
ሎት 3. የጽህፈት መሳሪያዎች cpo ብር (6,000)
ሎት 4. የኤሌክትሪክ እቃዎች cpo ብር (6,000)
ሎት 5. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች cpo ብር (8,000)
ሎት 6. የመኪና እቃዎች cpo ብር 5,000)
ሎት 7. ቋሚ የቢሮ እቃዎች cpo ብር (6,000)
ሎት 8. የጥገና እቃዎች (ቁልፎችና የመሳሰሉት) cpo ብር (5,000)
ሎት 9. የደንብ ልብስ ስፌት cpo ብር (3,000)
ሎት 10. የመድኀኒቶች ብር (8,000)
ሎት 11. ቋሚ የህክምና መሳሪያዎች ብር (10,000)
ሎት 12. የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች cpo ብር (5,000)
ሎት 13. የሻይ ቤት ጨረታ
አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማስገባት ይኖርበታል።
2. የግብር መክፈያ ግዴታዎችን የተወጡ መሆኑን የሚገልፅ ከግብር አስገቢው ባሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
3. ጨረታው በሚወዳደሩበት በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ መሆን አለበት
4. ማንኛውም ተጨራች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በዝርዝር በተግለጸው መሠረት ለየአንዳንዱ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገባ (በc.p.o) ብቻ በጤና ጣቢያው ስም አሰርተው ማስያዝ ይኖርበታል።
5. የተያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለተሸነፉ ድርጅቶች ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል
6. ጨራታውን ለአሸነፉ ድርጅቶች ደግሞ የጨረታውን ውል ማስከበሪያ ብር 10% አስይዘው እንደተፈራረሙ በጨረታ ማስያዥ የተያዘው ብር ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ ነገር ግን ለአሸነፊ ድርጅቶች ውል ፊርማው በወቅቱ እቃዎቹን የማየቀርቡ ከሆነ ከሰያዙት 10% ላይ 1% በየቀኑ የቅጣት ይቀነስባቸዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ በማይመለስ ለእያንደንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ መግዥ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ኮተቤ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 55 ግዥ ክፍል በአካል ቀርቦ የጨረታውን ሰነድ እያንዳንዱ በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይኖርባታል፡፡
8. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ አድራሻ፣ ፊርማ እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
9. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ መሠረት በማድረግ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙለት አንድ ኮፒ እና ኦርጅናል በታሸጋ ኢንቫሎፕ ውስጥ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጃምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 54 በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በአስራ አንደኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጓ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 (ሦስት ሰዓት ተኩል) ላይ ይከፈታል።
11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ጤና ጣቢያው የሚገዛቸውን እቃዎች 20% የመጨመር እና የመቀነስ መብት አለው፡፡
13. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ግዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 60 (ስልሳ ቀናቶች) እና ለተጨማሪ ቀን 28 (ሃያ ስምንተ) ቀናት ተጨማሪ ቀናቶች ይኖረናል፡፡
14. ተጫራቾች በፎቶ በምታቀርቡት ናሙና ላይ ማህተም የኮምፒውተር ጹሁፍ አትጸፉ ቀላል እስቲካር ተጠቀሙ።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0983079253 ወይም 0116734030 ወይም 0918123796 ደውለው ይጠይቁ።
አድራሻ:- ኮተቤ ጤና ጣቢያ 02 ወደታች በሚወስደው መንገድ 600 ሜትር ገባ ብሎ፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የኮተቤ ጤና ጣቢያ
