Tender Detail

Tender Details


የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ እስፔርፓርት፣ የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


የግልጽ እና የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ እስፔርፓርት፣ የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች በቀን 01/07/2018 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች፡ -

1.     ለግልፅ እና ለሀራጅ ጨረታ በዘርፍ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤

2.     ለሐራጅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤

3.     ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን (መግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል

4.     ለሐራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤

5.     ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፣

6.     ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃዎች ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፡፡

7.     ዕቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡

8.     በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤

9.     አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤

10. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡

11. ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፤

12. ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ ከቀን 01/07/2018 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በቀን 03/07/2018 ከረፋዱ 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤

13. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው በቀን 03/07/2018 ከረፋዱ 4:15 በቅ/ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤

 

N.B - አሸናፈው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender