Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የአራብሳ የመጀ /ደ/ት/ቤት
  • Address አራብሳ ኮንደምኒየም ጤና ጣቢያ አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116124026
  • Website
  • Deadline19 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-19 00:00:00
  • Categories Maintenance And Repair , Mechanical Work and Materials

በለሚ ኩራ/ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 4 የአራብሳ ቅድሚያና የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ግዢ የአራብሳ 1ኛ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት 2ኛ ዙር (002/2018) የሚያገለግሉ ሎት 1 የኤሌክተሮኒክስ ጥገና፣ ሎት 2 ሌሎች ጥገና ስራዎች፣ ሎት 3 የትምህርት እቃዎች፣ ሎት 4 ለህክምና እቃዎች፣ ሎት 5 የህትመት እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የአራብሳ የመጀ /ደ/ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በለሚ ኩራ/ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 4 የአራብሳ ቅድሚያና የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ግዢ የአራብሳ 1ኛ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት 2ኛ ዙር (002/2018) የሚያገለግሉ ሎት 1 የኤሌክተሮኒክስ ጥገና፣ ሎት 2 ሌሎች ጥገና ስራዎች፣ ሎት 3 የትምህርት እቃዎች፣ ሎት 4 ለህክምና እቃዎች፣ ሎት 5 የህትመት እቃዎች ተጫራቾች የሚከተሉትን የጨረታ መመሪያ ነጥቦች በመረዳት በጨረታ ሰነድ ላይ መግለፅ ይኖርባቸዋል ።

1.     ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2.     በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስተር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3.     የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።

4.     በተጨማሪ እሴት ታክስና ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን

5.     ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን ገንዘብ ሲፒኦ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6.     ከብራሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የታተመ ደረሰኝ መቅረብ የሚችል

7.     ለጥገና ስራዎች መልካም ስራ አፈፃፅም መቅረብ የሚችል

 

ሎት ቁጥር

የሎት ዝርዝር ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት

የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ ብር

ሎት 1

የኤሌክትሮኒክስ ጥገና

7,000

ሎት 2

ሌሎች ጥገና ስራዎች

15,000

ሎት 3

የትምህርት እቃዎች

8,000

ሎት 4

ለህክምና እቃዎች

5,000

ሎት 5

ለህትመት እቃዎች

8,000

 

8.     የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ /ለ1 ሎት/ የማይመለስ ብር በየሎቱ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 94 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ። በጥቃቅንና አነስተኛ ምርት ብቻ ከክፍያ ነፃ ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ ከፅ/ቤቱ ሀላፊ የተፈረመ እና ለሚያመርቱት ምርት /እቃ/ እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛት ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ።

9.     ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 94 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በማሸግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በዚያው እለት 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።

11. አሸናፊዎች ተጫራቾች አሸናፊነት እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ 10 ሲፒኦ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።

12. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።

13. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ትራንስፖርት በማጓጓዝ የመስሪያ ቤቱን ንብረት ክፍል ድረስ በማስገባት ማስረከብ ይኖርበታል።

14. ተጫራቾች ባሸነፉት እቃዎች ላይ መስሪያ ቤቱ 20 ፐርሰንት መቀነስ 20 ፐርሰንት የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው። መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አራብሳ ኮንደምኒየም ጤና ጣቢያ አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡- 0116124026

በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የአራብሳ የመጀ /ደ/ት/ቤት

Save Tender