በን/ስ/ላ/ክ/ከ የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚፈልጋቸውን ነገሮች ብቃት ያላቸውንና በመስኩ ከተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ
የሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 002/2018
በን/ስ/ላ/ክ/ከ የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚፈልጋቸውን፤
• ሎት 1 ደንብ ልብስ... 6,000.00
• ሎት 2 አላቂ የፅዳት እቃዎች ... 4,000.00
• ሎት 3 አላቂ የቢሮ እቃዎች ... 4,000.00
• ሎት 4 ቋሚ እቃዎች ... 10,000.00
• ሎት 5 መድኃኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት ... 9,900.00
• ሎት 6 ጥገና ... 15,000.00
• ሎት 7 የባዮ ሜዲካል የጥገና መሣሪያ እቃዎች ... 10,000.00
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ፡-
1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በመንግሥት ግዥ ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ -ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ የተመዘገቡ፤ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
2. ተጫራቾች የጨረታው ለእያንዳንዱ ሎት ለሚወዳደሩበት ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ ከላይ በሎት የተሰጡትን ማስከበሪያ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከተታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በየሎቱ በመክፈል በን/ስ/ላ/ክ/ከ የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ጀሞ ሚካኤል (አፍሪካ ሕንፃ) ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 53 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፤
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 53 ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን (በአስረኛው ቀን ) 11፡30 /አስራ አንድ ተኩል/ ይታሸጋል፤ በ11ኛው ቀን በቢሮ ቁጥር 53 አራት ሰዓት (4፡00) ታሽጎ ይከፈታል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሌሎች በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከቫት ጋር ያለውን ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፤
8. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም !
9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
አድራሻ፡- በን/ስ/ሳ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ጀሞ ሚካኤል (አፍሪካ ሕንፃ ) ፊት ለፊት ይገኛል።
ስልክ ቁጥር፡- 0972705152
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ
