Tender Detail

Tender Details

  • Company የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩኘ ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 19 20 33 68
  • Website
  • Deadline26 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-27 00:00:00
  • Categories Raw Materials , Cargo Vehicle , Vehicle

መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩኘ ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ


የጨረታ ማስታወቂያ

 

መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

•        ሎት 1፡- ተሽከርካሪ SINO TRUCK HOWO6X4 SHOWER TRUCK LHD

•        ሎት 2፡- Soldering Lead SPb60 Sn 40 EN 29453(Raw Material) እና Play wood 122cmx244cmx0.8mm

በመሆኑም ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ሎት 1 ተሽከርካሪ SINO TRuCK HOWO6X4 SHOWER TRUCKLHD፣ ሎት 2- Soldering Lead SPb60 Sn 40 EN 29453 (Raw Material) እና Play wood 122cmx244cmx0.8mm ግዥውን በግልፅ ጨረታ አወዳድረን ለመግዛት ስለምንፈልግ፤ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በመንግስት ዕቃ ግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡ የሆኑና፡-

1.     ማንኛውም ተጫራች አግባብነት ያለው በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የወቅቱን ግብር የከፈለ፤

2.     የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም እንደአስፈላጊነቱ ለኤክሳይስ ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል

3.     ተጫራቹ የተሰጠውን የጨረታ ቅጽ በአግባቡ መሙላት፣

4.     በጨረታ እንዳይሳተፍ በባለስልጣኑ ያልታገደበ መሆን፤

5.     የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል፤

6.     ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በማያሻማ ሁኔታ መግለፅና ሙሉ አድራሻቸውን መጥቀስ አለባቸው።

7.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ። ሰነዱም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ለ15 ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት ዝርዝሩን ሞልተው ማቅረብ ይችላሉ።

8.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% (በCPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

9.     ማናቸውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ አንድ ወጥ በሆነ በአራት ቅጅዎች ማቅረብ አለባቸው፡- 1ኛ ቅጅ ላይ ኦርጅናል ቴክኒካል ዶክመንት፤ 2ኛ ኦርጅናል ፋይናንሻል ዶክመንት፤ 3ኛ ኦርጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒ እና 4ኛ ኦርጅናል ፋይናንሻል ዶክመንት ኮፒ በማለት በሁለተኛው ቅጅ ላይ “ኮፒ” የሚል ምልክት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ማለትም ከ 05/06/2018 እስከ 19/06/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት አለባቸው።

10. ጨረታው በ20/06/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

11. ከእስፔሲፊኬሽን ውጭ የሆነ ዕቃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑም በላይ በዚህ ምክንያት ለሚደርሰው ኪሣራ ተጠያቂ ይሆናል።

12. የጨረታ ሰነዱ እና የጨረታ ሳጥኑ የሚገኘው አምቦ ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የሚገኘው ኢንዱስትሪያችን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ማግኘት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡-

የልማት ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የጨረታ ሰነዱ እና የጨረታ ሳጥኑ የሚገኘው ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 19 20 33 68/ 09 20 94 41 04/ 09 69 39 19 69 ወይም +251-11-219-00-42 ይደውሉ።

 

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩኘ ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ

 

Save Tender