Tender Detail

Tender Details


የሐምሌ፩ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት የተለያዩ ለት/ት ሥራ የሚውል የሠራተኛ የደንብ ልብስ፣ በሀገር ውስጥ የተሰራ የስፖርት መምህር ጫማ እና ቱታ፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የአላቂ የትምህርት እቃዎችን ተጫራቾችን አወዳድሮ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

ሐምሌ ፩ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት


የግዥ ማስታወቂያ

 

የሐምሌ፩ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት የተለያዩ ለት/ት ሥራ የሚውል የሠራተኛ የደንብ ልብስ፣ በሀገር ውስጥ የተሰራ የስፖርት መምህር ጫማ እና ቱታ፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የአላቂ የትምህርት እቃዎችን ተጫራቾችን አወዳድሮ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

ተጫራቾች፡-

•        በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣

•        በተጠቀሰው የስራ ዘርፍ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣

•        የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤

•        ተጫራቾች በየሎቱ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪ በCPO በትምህርት ቤቱ ስም በተጠቀሰው ሎት ለደንብ ልብስ፡- 5,000፤ ለአላቂ የቢሮ ዕቃዎች:- 6,000፤ ለአላቂ የትምህርት ዕቃዎች:- 4,000፤ ለአላቂ የፅዳት ዕቃዎች:- 5,000 የጨረታ ማስከበሪ ማስያዝ ግዴታ አለባቸው።

•        የአሸናፊ ተጫራች ማሸነፍ በተገለፀበት ከሰባት ቀን ጀምሮ ውል መፈፀምና 10% /አስር ፐርሰንት/ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል።

•        ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

•        ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጉ ዕቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባችኋል።

•        ተጫራቾች ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋ እና ሌሎች መረጃዎች በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።

•        ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል። ከስራ ቀን ዉጭ ከሆነ ግን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

•        መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበ ነው።

አድራሻ፡- ቦሌ ማተሚያ ጀርባ በሞሮኮ ባዝ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር:- 0115-57-44-63//011-5-57-26-81

 

የሐምሌ ፩ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት

Save Tender

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጥቅል 1 -- Kitchen Material ans hand tools (የኩሽ...

READ MORE
በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE