Tender Detail

Tender Details


በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሎሚ ሜዳ ጤና ጣቢያ የ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሎሚ ሜዳ ጤና ጣቢያ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 002/15952/2018 ዓ.ም

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሎሚ ሜዳ ጤና ጣቢያ የ2018 በጀት ዓመት የጨረታ ቁጥር 002/2018

   1. አላቂ የጽህፈት እቃዎች               ሎት.1 3,500.00

   2. የጽዳት እቃዎች                       ሎት.2 3,500.0

   3. የደንብ ልብስ                         ሎት.3 5,000.00

   4. ቋሚ እቃዎች                         ሎት.4 15,000.00

   5. ሕትመት ውጤቶች                   ሎት.5 2,500.00

   6. የሰው መድሃኒት                      ሎት.6 25,000.00

   7. ለሕንጻ ቁሳቁስ መግዣ               ሎት.7 2,000.00

   8. ለህንጻ ቁሳቁስ እድሳት               ሎት.8 10,000.00

 

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-

1.     የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችል።

2.     በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

3.     የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና በተሰጣቸው የንግድ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ ይኖርባቸዋል።

4.     የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5.     ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ከጤና ጣቢያው ረዳት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 49 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

6.     ማንኛውም ተጫራች ከታወቀ ባንክ የጨረታ ማስከበሪያ CPO በየሎቱ ስር የተጻፈውን ማቅረብ ይኖርበታል CPO የተሰላው ከሚገዛበት ዋጋ 0.5% ነው። ጥቃቅን እና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማራችሁበት የንግድ ሥራ መስክ/ዘርፍ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ።

7.     ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ60 ቀናት ብቻ ነው።

8.     የጨረታ አሸናፊዎች ውል ማስከበሪያ ለአሸነፈበት ዋጋ 10% CPO ማስያዝ ግዴታ አለበት። እንዲሁም ተጫራቹ እቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት እቃ ግምጃ ቤታችን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት 3፡00 5፡30 እና 7፡30-9፡30 ድረስ አቅርቦ ማስረከብ አለበት።

9.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዋናውን እና ኮፒውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ 11፡30 ሰዓት በመምጣት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የሞሉትን ዋጋ ከነሙሉ ሰነዱ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ10ኛው ቀን ልክ 11፡30 ሰዓት የሚያበቃ ሲሆን በ11ኛው ቀን በ 3፡30 ታሽጎ በዛው ቀን 4:00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።

10. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአንድ ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት።

12. ተጫራቾች በሚጫረቱበት እቃ ላይ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።

13. ተጫራቾች በጨረታው ላይ በተጫራች የሚሞሉ ክፍሎችን እና ዋጋ የሚሞላው ክፍል 4 እና ክፍል 6 የመሙላት ግዴታ አለባቸው።

 

አድራሻ፡- አጠና ተራ ሎሚ ሜዳ ጤና ጣቢያ ለበለጠ መረጃ፡- 011-2-73-86- 34/011-273-87-17

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሎሚ ሜዳ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender