በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች እና ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም እና ማሰራት ይፈልጋል።
የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው አይነት መደበኛ ጨረታ ቁጥር 2/2018
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች እና ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም እና ማሰራት ይፈልጋል።
1. ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች
2. የተለያዩ የመብራት ተጓዳኝ እቃዎች
3. ዘመናዊ የውሃ መፈሳሻ ተፋሰስ ግንባታ
4. የፖሊስ ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ኮርኒስ እና የአርማታ ስራ
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
1. በዘመኑ የታደሰ የህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
3. የግዥ መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም VAT፣ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ለዘመናዊ የውሃ መፋሰሻ ተፋሰስ ግንባታ እና ለፖሊስ ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ኮርኒስ እና የአርማታ ስራ በኮንስትራክሽን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የብቃት ማረጋገጫ ኦርጂናሉ ሊቀርብ ይችላል።
6. የጨረታ ስፔስፊኬሽን /ዝርዝር መግለጫ እና ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላሉ፤ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መግዥያ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለኮምፒውተር እና ተዛማጅ ለመብራት ተጓዳኝ እቃዎች እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ሰነድ በመግዛትና ዋጋ በመሙላት ማስገባት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለመብራት ተጓዳኝ እቃዎች 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/፣ ለዘመናዊ የውሃ መፋሰሻ ተፋሰስ ግንባታ 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/፣ ለፖሊስ ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ኮርኒስ እና የአርማታ ስራ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በC.P.O ከህጋዊ ባንክ ወይም በመሂ 1 ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው ልዩ ልዩ መረጃዎች ፎቶ ኮፒ አድርገው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል።
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ በገ/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን በግዥ ቢሮ ቁጥር 39 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለኮምፒውተር እና ተዛማጅ የመብራት እቃዎች እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 7፡45 ድረስ ሰነዱን ዋጋ ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል። እንደዚሁም ለፖሊስ አዳራሽ ማጠናቀቂያ ሰሪ እና ለዘመናዊ ተፋሰስ ግንባታ እስከ 22ኛው ቀን ከቀኑ 7፡45 ድረስ ሰነዱን ዋጋ ሞልተው ማስገባት አለባቸው፤
9. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ግዥ ቢሮ ቁጥር 39 ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተቆጥሮ የኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች እንደዚሁም የመብራት እቃዎች በ16ኛው ቀን 7፡45 ሰአት ታሽጎ 8፡00 ሰአት ላይ ይከፈታል። የተፋሰስ ግንባታ እና የስብሰባ አዳራሽ ኮርኒስና አርማታ ስራ በ22ኛው ቀን ከቀኑ 7፡45 ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡00 ሰአት ላይ ይከፈታል። የእቃውም ሆነ የግንባታው ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
10. ከላይ የተጠቀሰው ጨረታ አሸናፊው የሚለየው ለመ/ቤቱ በሚያስገኘው ጥቅም ይሆናል።
11. የጨረታው አሸናፊ ለሆነው ተወዳዳሪ እቃዎቹን አቅርቦ ወይም ግንባታውን አጠናቆ ክፍያ ሲፈጸምለት ከ20,000/ ሀያ ሺህ ብር በላይ ከሆነ 3% ዊዝ ሆልዲንግ ወይም የቅድመ ግብር ክፍያ የሚቀንስበት መሆኑን መታወቅ አለበት። እንደዚሁም ከግንባታ ክፍያ ላይ ለ1ዓመት በዋስትና የሚቆይ ሪቴንሽን 5% በመያዝነት ተቀንሶ ይቆያል በተጨማሪም በግንባታ ሰነድ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
12. የጨረታ ጊዜ/ሰአት ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ምንም አይነት ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይቻልም።
13. የቀረበው የዋጋ መወዳደሪያ ጨረታው ከተከፈተበት እለት አንስቶ ለ30 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ እና ከተጫራቾች መመሪያ ላይ ያገኛሉ እንደዚሁም ቢሮ ቁጥር 39 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0116 85 15 29/28 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን
