የሰንዳፋ በኬ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅቱ የማይጠቀምበት የሚያገለግሉ እና የማያገለግሉ ጀኔሬተሮች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የሰንዳፋ በኬ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅቱ የማይጠቀምበት የሚያገለግሉ እና የማያገለግሉ ጀኔሬተሮች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጸለን።
የመስሪያ ቤቱ አድራሻ፤ በሰንደፋ በኬ ከተማ አስተዳደር ዳሸን ባንክ ፊትለፊት በሰንዳፋ በኬ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት በመቅረብ የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ቲን ነምበር ቁጥር ያለቸው እንዲሁም የተጨማሪ ዕሴት ታከስ ተመዝጋቢና ምስከርወረቀት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
2 የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 እና ከሰዓት 7፡30-11፡00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
3. የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ጥር 1/5/ 2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 እና ከሰዓት 7፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ ጄኔረተር በሚገኝበት ቦታ ማየት ይችላሉ፡፡
4.ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15/5/ 2018 ዓ.ም
5.ጨረታው ጥር 16/5/ 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡50 ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡05 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ መነሻ ዋጋ 1 %የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በማዘጋጀትና ዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0116860068
የሰንዳፋ በኬ ውሃ እና ፋሳሽ አገልግሎት ድርጅት 5
