Tender Detail

Tender Details


ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ከታች የተገለፁትን አገልግሎቶች መስጠት እንዲችል፣ ልዩ ልዩ መድኃኒቶችን እና የሕክምና መገልገያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Hamlin Fistula Ethiopia (ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ)


ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ

 

     አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ    .

 

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት ችግር የሚገጥማቸውን እናቶች ከስድሳ አመታት በላይ የነፃ ሕክምና እየሰጠ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፣ ከነፃ ሕክምናው በተጨማሪ በሐምሊን የአዋላጅ ነርሶች ት/ቤት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ፤ እንዲሁም በቡራዩ ልዩ ዞን በሚገኛው የደስታ መንደር መልሶ ማቋቋም ማዕከል፡ በምንሰጠው ሕክምና ለዳኑና ተጨማሪ የቅርብ ክትትል ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የራስ-አገዝ የሙያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። 

በዚሁም መሠረት ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ከላይ የተገለፁትን አገልግሎቶች መስጠት እንዲችል፣ ልዩ ልዩ መድኃኒቶችን እና የሕክምና መገልገያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ጨረታው ከጥር 4፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 13፣ 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ተወዳዳሪ ድርጅቶች ዝርዝር የጨረታውን መመሪያ፣ እንዲሁም ግዢ የሚፈፀምባቸውን የሕክምና መገልገያዎች አይነትና ብዛት የሚገልፀውን ሰነድ፡ የማይመለስ ብር 250.00 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የፋይናንስና ግዢ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ይህንን ጨረታ በከፊል ወይንም በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ተወዳዳሪ ድርጅቶች ጨረታውን በተመለከተ ለሚያስፈልጋቸው ማናቸውም ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-371-65-44/45/46- የውስጥ መስመር 125/198/199 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ

ስልክ ቁጥር 011-371-65-44/45/46

Save Tender