በኢ.ፌ.ዲ. ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት በሀገር ውስጥ የሚፈፀሙ ለኢንዱስትሪው ሰራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካ እና ለሳሪስ ፓወር ፋክተር ኮሬክተር ማምረቻ ፋብሪካ የወተት አቅርቦት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ
ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ
-
- በኢ.ፌ.ዲ. ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት በሀገር ውስጥ የሚፈፀሙ ለኢንዱስትሪው ሰራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካ እና ለሳሪስ ፓወር ፋክተር ኮሬክተር ማምረቻ ፋብሪካ የወተት አቅርቦት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ተጋብዟችኋል።
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) ማስረጃ ማቅረብ አለበት
- ተጫራቾች በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስም በብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ (CPO)፣ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሎት- 1 6,772 (ስድስት ሺ ሰባት መቶ ሰባ ሁለት ብር ) እና ለሎት-2- 3,922 (ሶስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሁለት ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ለየብቻው ከሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለበት።
- ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢክፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ አንደኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቶች በገዙትና በሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፁትን ሆኔታዎች በአግባቡ በመጠቀም የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ የሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ በአንድ ኤንቨሎፕ አሽገው 2ኛ ፎቅ ላይ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራች ለጨረታ ሰነዱ ቴከኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዱን በአንድ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይዘጋል በዚሁም ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3ኛ ፎቅ ላይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
- ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 60 (ስልሳ) ተከታታይ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾችም ይህንኑ አውቀው ስለመቀበላቸው በቴክኒካል ኦርጅናል ሰነዳቸው ላይ ማረጋገጥ አለባቸው።
- ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም። ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ለቡ መብራት ኃይል ከጀነራል መርከንታይል አጠገብ
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን ስልክ፟፦ +251 912450566 +251 910 162733 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኢ.ፌ.ዲ. ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ
ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ
