በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን ለወግዲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የቢሮ ጥገና፣ የቀለም መቀባት ስራ( የውስጥና የውጭ) የማዋለጃ አልጋዎች አለሙንየም ፓርቲሽን ስራ ፤ለተለያዩ በርና መስኮት እድሳት እና ጥገና፣ተጨማሪ ከላሶች ግንባታ በ2018 በጀት ዓመት Susan Thompson Buffer Foundation በጀት በግለጽ ጨረታ አወዳድሮሁሉንምየግንባታማቴሪያሎችን፣ቀለሞች፣ የእጂ ዋጋውን ተቋራጩችሎ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን ለወግዲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን ለወግዲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የቢሮ ጥገና፣ የቀለም መቀባት ስራ( የውስጥና የውጭ) የማዋለጃ አልጋዎች አለሙንየም ፓርቲሽን ስራ ፤ለተለያዩ በርና መስኮት እድሳት እና ጥገና፣ተጨማሪ ከላሶች ግንባታ በ2018 በጀት ዓመት Susan Thompson Buffer Foundation በጀት በግለጽ ጨረታ አወዳድሮሁሉንምየግንባታማቴሪያሎችን፣ቀለሞች፣ የእጂ ዋጋውን ተቋራጩችሎ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፋ ንግድ ፈቃድ ያለው ማንኛውም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈረቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ማወዳደርየሚችሉ መሆኑን እንጋብዛን፣
1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም TIN ያላቸው፡፡
2. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
3. የግዥ መጠን 200,000.00 እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሰት ታከስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቀረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳትፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቀረበ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የንገድ ዘረፍ የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር500 ብር (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ወግዲ የመጀመረያ ደረጃ ሆል ግዥ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 24 ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም(ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የንግድ ዘርፍ የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው ፡፡ ቼከ ማስያዝ አይቻልም፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን (ሰነዱን) አንድ ወጥ በሆኖ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ወግዲ የመጀመረያ ደረጃ ሆ/ል ገዥ/ፋ/ን አስ/የስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥነ ውስጥ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይቻላል፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ውሎ በ22ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4:30 ላይ ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4:30 ላይ ይከፈታል::
8. ጨረታው የሚካሄደው በድምር (በሎት) ውጤት ነው::
9. የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድሰዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
10. ሆስፒታሉ ጨረታውን በሎት ወይም በድምር ወጤት የሚያወዳድር ሲሆን ከተዘረዘሩት ስራዎች ውስጥ ሳይሞሉ መተው አይቻልም፡፡
11. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን ሎት ውስጥ ሁሉንም ካልሞላ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡
12. በጨረታ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ከ5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈውን የግንባታ ጠቅላላ ዋጋ 10% የውለታ ማስከበሪያ በማስያዝ ውጩ መውሰድ አለበት፡፡
13. የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ግብር ያካተተ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ቫቱን ጨምራችሁ መሙላት አለባችሁ፡፡
14. ተጫራቾች በፖስታው ላይ የጨረታውን ቁጥር የሚጫረቱበትን የንግድ ዘርፍ፣ፌርማ ማህተምን መፃፍ አለባቸው ፡፡
15. በጨረታው በመሳተፍ የሚፈልጉ ሰለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ወግዲ የመጀመረያ ደረጃ ሆስፒታል በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334450553 ስልክ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
16. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
17. ጨረታው በመሰረዙ ምከንያት ተጫራቾች በጨረታው በመወዳደር ላወጡት ወጭመ/ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን፣
18. እያንዳንዱ ስራ በሚሰራበት ጊዜ በቀረበው እስፓስፍኬሽን መሰረት በማሃነድስ ተፈትሾ መሆኑን፣
19. ማንኛውም ተጫራቾ ዋጋ ለሞላ መ/ቤቱ ያወጣውን እስፓስፍኬሽን ሰርዞ የራሱን እስፓስፍኬሽን ከመፃፍ የለበትም ፤ይህን ካደረገ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
20. ማንኛውም ተጫራቾ አሸናፊ ከሆነ የእጅ ዋጋውንም ሆነ ሁሉንም ተፈላጊ የግንባታ ዕቃ አቅርቦት ተጫራቹ የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን ለወግዲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
