Tender Detail

Tender Details


በሮቤ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው የሚገኙ ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፣ ቆርቆሮዎች፣ የሶላር ባትሪዎች እና ሌሎች ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሮቤ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው የሚገኙ ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፣ ቆርቆሮዎች፣ የሶላር ባትሪዎች እና ሌሎች ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ማሟላት ይጠበቅበታል።

  1. ማንነቱን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመግዛት ከሮቤ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ያስገቡትን ዋጋ 20% /ሃያ በመቶ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ዕለት ጀምሮ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች በሮቤ ከተማ ግዥ ክፍል በመገኘት በስራ ሰዓት ማየት ይችላሉ።
  6. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት የጨረታው ሠነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዚሁ ዕለት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ እንደተረጋገጠ ያሸነፈበትን ዋጋ በሮቤ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት የባንክ አካውንት ላይ ሙሉ በሙሉ ገቢ ሲያደርግ ያሸነፈውን ንብረት በ5 ቀን ውስጥ ማንሳት አለበት።
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለበለጠ መረጃ ሮቤ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 09 34 86 64 74/ 09 12 36 52 94 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

 

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት

 

Save Tender