Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡- ሎት 01 የሲሚንቶ አቅርቦት፣ ሎት 02 የበር ስራ፣ ሎት 03 ኤጋ የጣራ ክዳን ቆርቆሮ፣ ሎት 04 ጠፈላማይ የገበሬ ማስልጠኛ ተቋም ጥገናና እድሳት ግንባታ፣ ሎት 05 የኩል መስክ እናቶች ማረፊያ ግንባታ፣ ሎት 06 የእንጃፋት እንስሳት ክሊኒክ ግንባታ፣ ሎት 07 ሃዋ ሚካኤል የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች መማሪያ ክፍል ግንባታ፣ ሎት 08 የማሽን ኪራይ ጨረታ፣ ሎት 09 የአርባቱ እንስሳ ውቅር ቤተክርስቲያን የብረት መጠለያ ስራ ጨረታ፣ ሎት 10 የፍትህ ቢሮ እድሳት /ጥገና/ ጨረታ በመደበኛና በተራድኦ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨ/መለያ ቁ/ግንአስ፡-062-/2018

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡- ሎት 01 የሲሚንቶ አቅርቦት፣ ሎት 02 የበር ስራ፣ ሎት 03 ኤጋ የጣራ ክዳን ቆርቆሮ፣ ሎት 04 ጠፈላማይ የገበሬ ማስልጠኛ ተቋም ጥገናና እድሳት ግንባታ፣ ሎት 05 የኩል መስክ እናቶች ማረፊያ ግንባታ፣ ሎት 06 የእንጃፋት እንስሳት ክሊኒክ ግንባታ፣ ሎት 07 ሃዋ ሚካኤል የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች መማሪያ ክፍል ግንባታ፣ ሎት 08 የማሽን ኪራይ ጨረታ፣ ሎት 09 የአርባቱ እንስሳ ውቅር ቤተክርስቲያን የብረት መጠለያ ስራ ጨረታ፣ ሎት 10 የፍትህ ቢሮ እድሳት /ጥገና/ ጨረታ በመደበኛና በተራድኦ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  1. በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሠረት የእያንዳንዱ ሎት የተናጠል በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነበር/ ሰርተፍኬት ያላቸውና፣ የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለሎት 01 ሲሚንቶ አቅርቦት፣ ሎት 02 የበር ስራ፤ ሎት 03 ኤጋ የጣራ ክዳን ቆርቆሮ የኢት.ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል እና ለሎት 04 የጠፈላማይ የገበሬ ማስልጠኛ ተቋም ጥገናና እድሳት ግንባታ፣ ሎት 05 የኩል መስክ እናቶች ማረፊያ ግንባታ፣ ሎት 06 የእንጃፋት እንስሳት ክሊኒክ ግንባታ፣ ሎት 07 ሃዋ ሚካኤል የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች መማሪያ ክፍል ግንባታ፣ ሎት 08 የማሽን ኪራይ ጨረታ፣ ሎት 09 የአርባቱ እንስሳ ውቅር ቤተክርስቲያን የብረት መጠለያ ስራ ጨረታ፣ ሎት10 የፍትህ ቢሮ እድሳት /ጥገና/ ጨረታ የኢት.ብር 350 /ሶስት መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.3 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎችና ግንባታዎች ለሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም ከባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /Unconditional Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከፖስታው ውስጥ አብሮ መግባት ወይም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል።
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ሎት 01 ሲሚንቶ አቅርቦት፣ ሎት 02 የበር ስራ፣ ሎት 03 ኤጋ የጣራ ክዳን ቆርቆሮ፣ ሎት 08 የማሽን ኪራይ ጨረታ ጠዋት 3፡45 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እንዲሁም የግንባታዎቹ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ የሚቆጠር 21 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ22ኛው ቀን ሎት 04 ጠፈላማይ የገበሬ ማስልጠኛ ተቋም ጥገናና እድሳት ግንባታ፣ ሎት 05 የኩል መስክ እናቶች ማረፊያ ግንባታ፣ ሎት 06 የእንጃፋት እንስሳት ክሊኒክ ግንባታ፣ ሎት 07 ሃዋ ሚካኤል የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች መማሪያ ክፍል ግንባታ፣ ሎት 09 የአርባቱ እንስሳ ውቅር ቤተክርስቲያን የብረት መጠለያ ስራ ጨረታ፣ ሎት 10 የፍትህ ቢሮ እድሳት /ጥገና/ ጨረታ ጠዋት 3፡45 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  5. የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይተላለፍና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን ኮፒና ኦርጅናል በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ስዓት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  7. አሸናፊው አካል እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል።
  8. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  9. ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም፤ ውድድሩ በየሎት ምድብ ጥቅል ብር ወይም ድምር ስለሆነ የሁሉም እቃ ዋጋዎች መሞላት አለበት፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  11. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች 033 336 01249፣ 0913669714 ወይም 0913871466 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender