Tender Detail

Tender Details


ሰላም የሕፃናት መንደር ኮምፒዩተሮች እና የቢሮ ማሽነሪዎችን ከነመለዋወጫቸው በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሰላም የሕፃናት መንደር


 

ሰላም ሕፃናት መንደር

ኮምፒዩተር እና የቢሮ ማሽነሪዎች ከነመለዋወጫቸው ለመግዛት የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ሰላም የሕፃናት መንደር ኮምፒዩተሮች እና የቢሮ ማሽነሪዎችን ከነመለዋወጫቸው በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ የዘመኑን የታደሰ እና ሕጋዊ ፈቃድ እንዲሁም ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች በሙሉ ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው በዝርዝር በተገለጸው ቀናት ውስጥ የመጫረቻ ሰነዳቸዉን ሞልተው ማቅረብ ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከህዳር 18/2018 ዓ/ም ጀምሮ 07 የሥራ ቀናት እስከ ህዳር 26 /2018 ዓ/ም ድረስ የማይመለስ ብር 1000 ብር (አንድ ሺህ ብር) በሠላም የሕፃናት መንደር ንግድ ባንክ መገናኛ ቅርንጫፍ ሂሣብ ቁጥር 1000005058558 ገበ በማድረግ ህጋዊ ደረሰኛቸውን በየካ ክፍለ ከተማ ከሚገኝ ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት የካ ሐና ማርያም ከፍ ብሎ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  2. የጨረታ ሰነዱን ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት የፋይናንስና የሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ ማግኘት ይቻላል።
  3. ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው መሠረት የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን መመሪያ ያልተከተለ ተጫራች ከውድድር ሊታገድ ይችላል።
  5. እያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነድ የቴክኒክ እና የፋይናንሽያል ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት።
  6. እያንዳንዱ ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) 250,000 ብር (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺ ብር) እና የአፈፃፀም ዋስትና 5% ከጠቅላላው የግዥ ገንዘብ የባንክ ማስያዣ ከመጨረቻ ሰነዳቸው ጋር ወይም ለብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል።
  7. ተጫራቾች ከህዳር 18/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ህዳር 25/2018 ዓ/ም ለተከታታይ 07 ቀናት ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ገዝተው በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው ህዳር 26/2018 ዓ/ ም ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት በተቋሙ የሠላም ህፃናት መንደር ዋናው መስሪያ ቤት አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
  9. ሰላም ሕፃናት መንደር ወይም ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911693673/0996525252/0911897199 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

 

 

Save Tender

Development Bank of Ethiopia extends the deadline for Rack-Mountable 2KVA UPS (Lot-1), IBM TS-4300 T...

READ MORE
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሎት1.የተለያዩ የህትመት ወረቀቶች፣ የተለያዩ ለህትመት የሚሆኑ ቀለሞች፣ ፎቶፎሊመር ፕሌት እና ኒሜራቶር በጨረታ አወዳድሮ መግ...

READ MORE
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር የኮምፒውተርና ተዛማች እቃዎች ግዥ

READ MORE
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ቁጥር NCB/06/2019 ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግል ታብሌቶችን ከህጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

READ MORE