በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የአሳግርት/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በሎት 1 የግንባታ ማቴሪያል እና በሎት 2 ለመንገድ ሥራ የሚያገለግሉ የማሽነሪዎች ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ/ዞን የአሳግርት ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 002/2018
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የአሳግርት/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በሎት 1 የግንባታ ማቴሪያል እና በሎት 2 ለመንገድ ሥራ የሚያገለግሉ የማሽነሪዎች ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታ ለመወዳደርየምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዛው የዕቃዎችና የሥራ ዝርዝሩን ዓይነት መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለትም በሎት 1 የግንባታ ማቴሪያል ብር 25,000 /ሃያ አምስት ሺ ብር/ እና በሎት 2 ለመንገድ ሥራ የሚያገለግሉ የማሽነሪዎች ኪራይ ብር 50,000 /አምሳ ሺ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በደብዳቤ የተረጋገጠ የሚሰጥ ዋስትና፣ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት ጽ/ቤቱ አሸናፊነቱን ከገለፀለት ቀን ጀምሮ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በውሉ መሰረት ዕቃዎቹን ወዲያው ማቅረብ እና ማሽኖቹን አስገብቶ ሥራ መጀመር አለባቸው።
- በተጫራቾች የተሞላ የጨረታ ሠነድ መቤቱ ሰነዱን እንዲሸጥ ባስቀመጠው ከ15/3/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በመ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማንኛውም የሥራ ሰዓት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /በሰም ባይታሸግም ዋናና ቅጂ በማለት ሙሉ አድራሻ በመፃፍ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ16ኛው ቀን ማለትም 30/03/2018 ዓ.ም የጨረታው ሣጥን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በተከታዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሎት የተገለፀውን ሰነድ ከአሳግርት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመሄድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ ንብረት አሳግር ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ድረስ ወይም በሰነዱ ላይ በተገለፀበት ሳይት ማቅረብ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢያንስ ለ2 ወር የጊዜ ገደብ ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡
- ለኢንተርፕራይዞች ከሥራና ሥልጠና ጽ/ቤት የሚቀርብ ማንኛውም የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም ።
- ለአሸናፊውም ድርጅት ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ የማይከፈል ሲሆን እቃውን አጠቃሎ ሲያስገባ ሙሉ ክፍያ የሚከፈለው መሆኑ እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው ድርጅት ጥራት ያለው እቃ በወቅቱ አስገብቶ እና ሂሳቡን በወቅቱ የሚያፀድቅ መሆን አለበት።
ውድድሩ በሎት ስለሆነ ማንኛውም ተወዳዳሪዎች በሎት ውስጥ የተዘረዘሩት ሁሉ እቃዎች ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0116240394 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
ወረዳው የሚገኝበት ርቀት ከአዲስ አበባ በ125 ኪ.ሜ እና ከደ/ብርሃን በ74ኪ.ሜ ላይ ይገኛል።
በሰ/ሸዋ /ዞን የአሳግር ወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤት
