Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አባይ ባንክ 1ኛ ፎቅ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0335520883
  • Website
  • Deadline08 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2 %
  • opening date2025-12-09 00:00:00
  • Categories Building Materials , Spare Parts

በአብክመ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሀርቡ ከተማ የ2018 በጀት አመት የተሽከርካሪ መለዋዎጫ እና ካሊብሬሽን የሚዛን ማነፃፀሪያ/ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአብክመ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሀርቡ ከተማ የ2018 በጀት አመት የተሽከርካሪ መለዋዎጫ እና ካሊብሬሽን የሚዛን ማነፃፀሪያ/ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የመኪና መለዋዎጫ

ሎት 2 ካሊብሬሽን /የሚዛን ማነፃፀሪያ/ - የግንባታ ማቴርያል

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫቾራች መወዳደር ይችላሉ

1. የጨረታ መለያ ቁጥር ሀር/ገ/ግ/ፋ/003/2018

2. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና መረጃውን ኦሪጅናልና እና የማይመለስ ኮፒ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ ይኖርበታል።

3. የግዥ መጠኑ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።

4. የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን / ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 15/03/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 29/03/2018 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ሀ/ከ/ አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ዓባይ ባንከ አንደኛ ፎቅ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 ብር በጥሬ ገንዘብ በመከፈል የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) የያዘ የጨረታ ሰነድ መግባት የሚችሉ ሲሆን ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ ነው።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቶቹ ለየብቻ በመለየት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 % ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማሲያዝ አለባቸው:: የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ በቢድቦንድ ከሆነ ከ60 ቀን ያነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ ተቀባይነት የለውም።

7 አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀናት ጀምሮ ካሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ በየሎቱ 10% በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡

8. የጨረታ ውድድር የሚያካሄደው በሎት ወይም በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም (እቃ) መኖር የለበትም፡፡

9. ተጫራቾች በየሎቱ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ሰነድን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ዓባይ ባንከ ıኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በቀን 30/03/2018 ዓ.ም 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው ዕለት የማይገኙ ከሆነ በሌሉበት ይከፈታል።

10, ውድድሩ የሚካሄደው በየሎቱ ጠቅላላ ድምር ነው፡፡

11. የጨረታ መከፈቻ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን እና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

12. ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ሲያጋጥም በፊርማ ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል።

13 መ/ቤቱ ካሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ካሸነፈው እቃ ወይም ገንዘብ መጠን ላይ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ተጫራቾች ክልሉ ላወጣቸው የግዥ አፈጻጸም መመሪያዎች ተገዥ መሆን ሲኖርባቸው ማሸነፉ ከተነገረ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራስን ማግለል አይቻልም።

15. አሸናፊ ድርጅት ንብረቱን በሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ግዴታ ይሆናል፡፡

16. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡

17. አሸናፊው ተጫራች ኦርጅናል እቃዎችን የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን እቃዎቹን የምንቀበለው በሚመለከተው ባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡

18. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ሀርቡ ከተማ አስተዳደርግ/ፋ/ን/አስ/ ዓባይ ባንክ አንደኛ ፎቅ ላይ በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 0335520883 /0921031272 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በእብከመ ደ/ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስተዳደር ቡድን

ማሳሰቢያ፦ በማንኛውም ሁኔታ የተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በሚከፈትበት ሰዓት የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡

የአብክመ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender