Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ልማት ማህበር
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0926277854
  • Website
  • Deadline06 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-06 00:00:00
  • Categories Construction Works , Contractors

የሲዳማ ልማት ማህበር በይርጋዓለም ፍልውሃ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የመዋኛ ገንዳ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ልማት ማህበር


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሲዳማ ልማት ማህበር በይርጋዓለም ፍልውሃ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የመዋኛ ገንዳ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት -

  1. ደረጃቸው GC-6/BC-6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተቋራጮች 2017 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ወይም ክልል ኮንስትራከሽን ባለስልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ የሚችሉ።
  3. ከዚህ በፊት በተለያዩ ፕሮጀክቶችን ውል ገብተው ግንባታ በመስራት ልምድ እና መልካም አፈጻጸም ያላቸው መሆኑን የሚገልጽ ከሁለት በላይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ክፍተት ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው እና ይህንኑ የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከተመዘገበበት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፈቃዳቸውን እና ተዕታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ወደ ሲዳማ ልማት ማህበር በኢትዮትጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000013477055 ገቢ በማድረግ በሲዳማ ልማት ማህበር ፋይናንስ እና አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURANTEE/ ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክከለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  8. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታውን ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
  9. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security) & ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ (ኮፒ) እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ (ኮፒ) ሰነዶችን በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፓስታ ውስጥ ተከተው በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6:00 ሰዓት በሲዳማ ልማት ማህበር ፋይናንስ እና አስተዳደር ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
  11. አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል።
  12. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
  13. አሠሪው መሥሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

 

ሲዳማ ልማት ማህበር

ሀዋሳ

 

Save Tender