በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጸ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መሰረተ ልማት የሚሰሩ ማሽነሪዎችን እና መኪናዎችን ለመከራየት ይፈልጋል።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጸ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ፡- መሰረተ ልማት የሚሰሩ ማሽነሪዎችን እና መኪናዎችን ለመከራየት ይፈልጋል፣
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ (መረጃዎችን በማቅረብ/ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘረፉ ህጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፍሉ።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለያብቻ በታሽገ ኤንቨሎፕ/ በፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ (ተዘግቶ) ልክ በዚሁ ቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል ፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ከልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም-
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበረያ ዋሰትና ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /C.P.O/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባችዋል ::
- ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቻው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቻው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪ ካላስያዙ የጨረታ ማስከብሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ለይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሸል ወይም ጨረታውን ትቻለዉ ማለት አይችልም፡፡
- ጽ/ቤታችን የሚያጫርታቸዉን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈለጊነታቸው እስከ (20%) በመጨመር ወይም በመቀነስ መግዛት ይችላል፡፡
- የመወዳደሪያ ሰነዱ በጨረታ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011439-94-93 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
