Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የ2018 በጀት ዓመት የቢሮ አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ)


 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር LHR/A/NCD/001/2018 ዓ.ም

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የ2018 በጀት ዓመት የቢሮ አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሚገዛው ዕቃ ተዛማጅ አገልግሎት

  • ሎት1 ፡- የተለያዩ አላቂ የፅህፈት መሣሪያዎች ግዥ
  • ሎት 2፡- ኮምፒውተር፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ
  • ሎት 3:- የፎቶ ኮፒና ፕሪንተር ቀለሞች ግዥ
  • ሎት 4፡- የደንብ ልብስ ግዥ
  • ሎት 5፡- የመኪና ጌጣጌጥ እና ታፕሴሪ
  • ሎት 6፡- የፅዳት እቃዎች ግዥ
  • ሎት 7፡- ሌሎች የቢሮ መገልገያ እቃዎች ግዥ
  • ሎት 8፡- የህትመት ግዥ
  • ሎት 9:-  የቢሮ ፈርኒቸር ግዥ
  • ሎት 10፡- የመኪና ኪራይ
  • ሎት 11፡- የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ
  • ሎት 12፡- የጄኔሬተር እና ኤሲ ጥገና እና ሰርቪስ
  • ሎት 13፡ ላተራል ፋይሊንግ ካቢኔት ግዥ

በመሆኑም በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1፡- 3000 ብር/ ሶስት ሺ ብር/፣ ለሎት 2፡- 5,000 /አምስት ሺ ብር/፣ ለሎት 3፡- 5,000 ብር /አምስት ሺ ብር/፣ ለሎት 4፡- 2500 ብር /ሁለት ሺ አምስት መቶ ብር/፣ለሎት 5፡- 4500 ብር/ አራት ሺ አምስት መቶ ብር/፣ ለሎት 6፡- 2000 (ሁለት ሺ ብር/፣ ሎት 7፡- 2500ብር /ሁለት ሺ አምስት መቶ ብር/፣ ለሎት 8፡- 5000 ብር/ አምስት ሺ ብር/፣ ሎት 9፡-30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/፣ ሎት 10፡- 5,000 ብር/አምስት ሺ ብር/፣ ሎት 11፡- 2,000 /ሁለት ሺ ብር/፣ ሎት 12፡- 20,000 /ሀያ ሺ ብር/፣ ሎት13፡- 60,000 /ስልሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ መሬት ይዞ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ስም አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፓርት እስከ ኤጀንሲው እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ፋይናንስ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም ቴከኒክ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ትክክለኛውን ቅጅ ለየብቻው በፓስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቁት እቃዎች ከጨረታው መክፈቻ ቀደም አድርገው ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ከተጠቀሰው ቀን ዘግይቶ የሚቀርብ ናሙና ተቀባይነት አይኖረውም።
  7. የጨረታው ፋይናንስ ሰነድ የሚከፈተው እና ግምገማ የሚካሄደው ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተመለከቱት ቴክኒካል መረጃዎች እና የእቃው ናሙናዎች በትክክል ተሞልቶ መቅረባቸው ሲረጋገጥ ነው፡፡
  8. ተጫራቾች ይህ ማስታቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 እና ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ኤም. ኤ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ የኤጀንሲው የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት በመምጣት የማይመለስ 300 ብር /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  9.  ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  10. ኤጀንሲው አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
  11. በለሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይቻልም።
  12. ኤጀንሲው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ

ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ኤም. ኤ ህንፃ 13ኛ ፎቅ ወይም በስልክ ቁጥር 011 812 5085 ደውለው ያነጋግሩ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ

 

Save Tender