ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሚከተሉትን ባትሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የሚፈልግ በመሆኑ ፍላጎቱ ያላቸው ግለሰቦች /ድርጅቶች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
My Wish Enterprise (ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር)
MY WISH ENTERPRISE
የተለያዩ ባትሪዎችን ለመሸጥ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሚከተሉትን ባትሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የሚፈልግ በመሆኑ ፍላጎቱ ያላቸው ግለሰቦች /ድርጅቶች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
|
ተ.ቁ |
የባትሪው አይነት |
ብዛት |
መነሻ ዋጋ ተ.እ.ታ. ጨምሮ |
|
1 |
12V 160 Ah SMF ESAN Battery |
64.00 |
41,387.59 |
|
2 |
12V 50 Ah JIS ESAN Battery |
88.00 |
12,933.63 |
|
3 |
12V 50Ah ESAN Battery |
40.00 |
11,085.97 |
|
4 |
12V 65Ah JIS ESAN Battery |
60.00 |
17,368.01 |
|
5 |
12V 70AH ESAN Battery |
77.00 |
17,552.77 |
|
6 |
12V 25Ah ESAN Battery |
30.00 |
7,390.64 |
|
7 |
112V 125 Ah SMF ESAN Battery |
440.00 |
32,149.29 |
- ተጫራቾች ከኅዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ኅዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ከለቡ መብራት ሃይል ወደ ኃይሌ ጋርመንት በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ዋና መ/ቤታችን በመምጣት ባትሪዎቹን መመልከት፤ የተጫራቾች መመሪያና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
- ተጫራቾች በሁሉም ወይም በከፊል የባትሪ አይነቶች ላይ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ለእያንዳንዱ የባትሪ አይነት የሚገዙትን ብዛትና አንዱን ባትሪ የሚገዙበትን ዋጋ /ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ/ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ መሙላት ይኖርባቸዋል።
- ስርዝ ድልዝ ያለበት መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም። ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች ለሚገዙት ባትሪ ያቀረቡትን መጫረቻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በማሰራት ከሞሉት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ተጫራቹ በተናጥልና በጥቅል ያቀረበው ዋጋ፤ የሚገዛው ብዛትና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን ዝርዝር ሁኔታዎችን ያካተተ ነው።
- ጨረታው ኅዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከመብራት ሃይል ወደ ኃይሌ ጋርመንት በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ዋና /ቤት
ለበለጠ መረጃ፡ በ 0911-31 88 56 ወይም 0911-99 35 55 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
