በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን በመደበኛ በጀት እና በስፖርት ምክር ቤት በጀት በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአብክመ የደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን በመደበኛ በጀት እና በስፖርት ምክር ቤት በጀት በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ለዚህም፡-
- ሎት 1 - የስፖርት ትጥቅ፣
- ሎት 2 - የጽሕፈት መሳሪያ፣
- ሎት 3 - የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 4 - ክሎሪን፣
- ሎት 5 - የመኪና ጎማዎች፣
- ሎት 6 – የመኪና እቃዎች፣
- ሎት 7 – ኤሌክትሮኒክስ፣
- ሎት 8 – ቋሚ እቃዎች፣
- ሎት 9 - የግንባታ እቃዎች፣
ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ለማቅረብ በዘርፉ የተሰማራችሁ አቅራቢዎች፡-
- በዘመኑ የታደሰ ተዛማጅ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው፤
- የግዥ መጠን ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የሚገዛውን እቃ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች እያንዳንዱን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤታችን በወሰነው የጨረታ ዋስትና ማለትም ሎት 1 - የስፖርት ትጥቅ 15,000፣ ሎት 2 - የጽሕፈት መሳሪያ 65,000፣ ሎት 3 - የጽዳት እቃዎች 10,000፣ ሎት 4 - ክሎሪን 10,000፣ ሎት 5 - የመኪና ጎማዎች 30,000፣ ሎት 6 - የመኪና እቃዎች ለእያንዳንዱ መኪና 10,000፣ ሎት 7 – ኤሌከትሮኒክስ 65,000፣ ሎት 8 - ቋሚ እቃዎች 10,000፣ ሎት 9 - የግንባታ እቃዎች 15,000 በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፤ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ ደረሰኝ በመቁረጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የሚያስይዙትም የዋስትና አይነት ቢያንስ ለ90 ቀናት የሚቆይ መሆን አለበት።
- የጨረታ ዋጋ ጸንቶ የሚቆየውም ይህ ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ለ40 ቀናት ይሆናል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ያልተሞላበት ክፍት ቦታ ካለ፤ ጨረታ ሰነዱ በፍሉድ ከተነካ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ካለ እና ፓራፍ ካላደረጉ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ቀን በአካል የማይገኙ ከሆነ በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው የሚከፈትበትን ሰዓት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን መረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው የድርጅቱን ማህተም በሁሉም ኮፒዎች ላይ በመጠቀም እና የጨረታ ሀሳባቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ዋና እና ኮፒውን በማያያዝ በጥንቃቄ በ2 ፖስታ በማሸግ በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በማስገባት ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በይፋ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚሸጠውን የጨረታ መመሪያ መመልከት ይችላሉ። እንዲሁም ወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በግንባር በመቅረብ እንዲሁም ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033-1-16-01-99/54 ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝብ በዓላት ቀን ከሆነ ወደፊት ባለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳስባለን።
- ተጫራቾች መ/ቤቱ ናሙና ላስቀመጠላቸው እቃዎች ብቻ በናሙናው መሰረት ያሸነፉትን እቃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
አብክመ የደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
