በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለገላን ክ/ከተማ ለማዘጋጃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪ እና መኪና አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለገላን ክ/ከተማ ለማዘጋጃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪ እና መኪና አወዳድሮ ማስጠገን ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ መረጃዎች በማቅረብ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፍ ይጋብዛል።
-
- በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- አቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
- ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ከትራንስፖርት ቢሮ የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ (ሰርተፊኬት) እና ደረጃ 2 (ሁለት)ፍቃድ ያለው መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ በሚፈልግበት ቦታ (መኪና ወይም ማሽነሪዎቹ ተበላሽቶ የቆሙበት ቦታ) ሄዶ መጠገን ወይም መሥራት የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት እና በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 2000.00 (ሁለት ሺህ) ብር በገላን ክ/ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከገላን ከ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ (ተዘግቶ) ልክ በዚሁ ቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ / CPO / ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10 % በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
- የመወዳደሪያ በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 4 45 01 82 በመደወል እና በአካል ተገኝቶ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት
/ገላን/
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት
