Tender Detail

Tender Details

  • Company Berhan Bank S.C (ብርሃን ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116185683
  • Websitehttps://berhanbanksc.com/
  • Deadline04 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው የገንዘብ መጠን አልተገለጸም።
  • opening date2025-11-04 00:00:00
  • Categories Lead Glass And Mirror

ብርሃን ባንክ አ.ማ ያገለገሉ መስታወቶች ባሉበት ሁኔታ በጥቅል ለማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

Berhan Bank S.C (ብርሃን ባንክ አ.ማ)


 

ያገለገለ የመስታወት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ፕ/ማ - 03/18

 

ብርሃን ባንክ አ.ማ ያገለገሉ መስታወቶች ባሉበት ሁኔታ በጥቅል ለማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረነውን ያገለገሉ መስታወቶች የጨረታ መነሻ ዋጋቸው እና የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሰነድ በዝርዝር ተቀምጧል።
  2. መስታዉቶቹ ጎማ ቁጠባ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ቅጥር ጊቢ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በማንኛውም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ቦሌ፣ ቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ በመገኘት ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበረያ ገንዘብ በC.P.O ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች መስታዉቶቹን ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ C.P.O ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ስዓት እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቦሌ፣ ቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
  6. ጨረታዉ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በፕሮፐርቲ እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል።
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያገለገሉትን መስታወቶች ለመግዛት ያቀረቡትን ዋጋ በመክፈል አሸናፊነታቸዉ በተገለፀላቸዉ በአምስት ቀናት ዉስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
  9. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን ሊሰርዝ ይችላል።

 

ተጨማሪ መረጃ ከፈልጉ በስልክ ቁጥር

0116631729 ደውለው ማግኘት ይችላሉ /ብርሃን ባንክ አ.ማ./

 

Save Tender