Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ቢሾፍቱ
  • Address ቢሾፍቱ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114338557
  • Website
  • Deadline03 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security187,508.00 (አንድ መቶ ሰማኒያ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ስምንት ብር)
  • opening date2025-11-03 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Animals , Animal Feed And Supply

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ በቢሾፍቱ ከተማ ለሚገኘው እንስሳት ምርምር እና እርዳታ ማዕከል በ2018 ዓ.ም ለከብቶች መኖነት የሚያገለግሉ የተለያዩ መኖዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ቢሾፍቱ


 

የጨረታ ማስታወቀያ

የጨረታ ቁጥር እ/ህ/ግ/ኮ 002/2018

 

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ በቢሾፍቱ ከተማ ለሚገኘው እንስሳት ምርምር እና እርዳታ ማዕከል በ2018 ዓ.ም ለከብቶች መኖነት የሚያገለግሉ የተለያዩ መኖዎች ግዥ የወጣ ግልፅ ጨረታ ነው።

ስለሆነም፣

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸዉ እንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የታከስ ከፋይ (Tin No) የምስክር ወረቀት ፤ የአቅራቢዎች ምዝገባ /suppiler list/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር (187,508.00) አንድ መቶ ሰማኒያ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ስምንት ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ /የባንክ ዋስትና/ ማስያዝ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንሰሳት ሕከምና እና ግብርና ኮሌጅ ግዥ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘውን ሰነድ እንድ ቴከኒካል ኦርጅናልና አንድ ቴክኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና እንድ ፋይናንሽያል ኮፒ በእናት ፖስታ በማድረግ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛዉ ቀን 7፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኮሌጁ ግዥ ከፍል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው መዝጊያ ሰዓት ታሽጎ በግልጽ ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይስተጓጎልም፡፡
  8. ተጫራቾች የአሸነፏቸውን አቅርቦቶች በሚሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
  9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ስልክ ቁጥር፡- 0114338557/0912065392

 

የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ

ቢሾፍቱ

 

Save Tender