Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
  • Address ባህርዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-222-11-00
  • Website
  • Deadline03 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋውን 1%
  • opening date2025-11-03 00:00:00
  • Categories Rent , Construction Machinery , Construction Vehicle

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ 2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ስራ የሚያስፈልጉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)


 

ድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ

የጨረታ ቁጥር 07/2018 ዓ/ም

 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ 2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ስራ የሚያስፈልጉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የሰርቪስ መኪና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ያልሆኑ መወዳደር ይችላሉ፤
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች ከጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው።
  6. የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% ለማሽነሪ ሆኖ ለሰርቪስ መኪና በቀን ግልባጭ መኪና በሰዓት፣ ለውሃ ቦቴ በሰዓት ለግልባጭ መኪና በሜ.ኩብ እና ሎቤድ በኪ ሜትር ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮንስትራሽን ኤጀንሲው ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ግቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኮፒውን ማስያዝ አለባቸው።
  8. ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ 09/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ - 24/02/2018 ዓ.ም ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን ፋይናንሻልንና ቴክኒካሉን ሰነዳቸውን በአግባቡ በመጠረዝ በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ በሁለት ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ ተበሎ ተዘጋጅቶ ከግዥ አፊሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ- 09/02/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንስትራክሽን ኤጄንሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወይም ከግዥ አፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በ24/02/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  11. የዋጋ መሙያ ቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ እና ፍቀት ካለው ፊርማ ያለው ቢሆንም ስርዝ ድልዝ ባለው ቦታ ላይ ከጨረታው ውድድር ውጭ ይደረጋል።
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 058-222-11-00 በመልከ ወይም በስልክ ቁጥር 058-320-55-55 ወይም 058-222-11-07 በመደወል ወይም በኤጀንሲው ድረ ገጽ www. arrca.gov.et ማግኘት ይችላሉ።

 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

ባህርዳር

 

Save Tender