በኢፌዲሪ ኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሽን ማምረቻ ኢንዱስትሪ Belt & pully, Electrical item & others, Vehicle spare parts, Oil, Greas & Chemical ግዢ በጨረታ አወዳድሮ መፈጸም ይፈልጋል።
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ኮማማኢ/ሰቼ ማ/02/2018
በኢፌዲሪ ኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሽን ማምረቻ ኢንዱስትሪ
የግዥ አይነት፡- Belt & pully, Electrical item & others, Vehicle spare parts, Oil, Greas & Chemical
የተጫራቾች መመሪያና ግዴታ
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ዋጋ VAT ጨምሮ ብር 2% በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ሲፒኦ (CP.O) ወይም የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫሪቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡት ከዚህ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ ይሆናል፤ በዋጋ መሙያ ቅፅ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ እጅግ የተከለከለ ነው።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
- የመወዳደሪያ ሰነዱን የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር ከ0/100) በመክፈል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ትይዩ በሚገኘው ጠማማ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 አንደኛ ፎቅ ላይ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በቀረበው ዝርዝር በመሙላት የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ ኢንዱስትሪው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ::
- የጨረታ ማስገቢያ ቀንና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚቀርብ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን በሕዝብ በዓላት ቀን ከዋለ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ በዓሉ በዋለ በማግስቱ ይሆናል::
- ጨረታው ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት በጨረታ ሰነድ ላይ የሚጠቀስ ይሆናል::
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለፀበት በኋላ በሦስት ቀን ውስጥ ቀርቦ ውል በመዋዋል ንብረቱን በኢንዱስትሪው ቅጥር ግቢ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦርጅናሉንና ኮፒውን ለየብቻ በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- አድራሻ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ትይዩ በሚገኘው ጠማማ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 አንደኛ ፎቅ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0940816206/0911769812 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ::
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ
የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
