Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa Traffic Management Authority (AATMA) (የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን)
  • Address ሃያ ሁለት መክሊት ሕንፃ 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10-01 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251116672279
  • Websitehttps://aatma.gov.et/
  • Deadline30 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-30 00:00:00
  • Categories Software & Applications Development , Software Provision, Development And Web Design

የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ መከታተያ እና መቆጣጠሪያ ሲስተም መተግበሪያ /ሶፍትዌር/ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Addis Ababa Traffic Management Authority (AATMA) (የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡- አአትማባ/ብግጨ/አገልግሎት/03/2018

 

የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ መከታተያ እና መቆጣጠሪያ ሲስተም መተግበሪያ /ሶፍትዌር/ ግዥ ጨረታ የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ መከታተያ እና መቆጣጠሪያ ሲስተም መተግበሪያ /ሶፍትዌር/ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች:-

  1. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡30 ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10-01 መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለሚያቀርቡት አገልግሎት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) ተመላሽ የሚሆን 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው።
  4. የጨረታው አሸናፊ ሆነው የተመረጡት ድርጅቶች የጨረታው ውጤት በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በአስር የስራ ቀናት ውስጥ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ዋና ክፍል በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% የመልካም ስራ አፈጻጸም በማስያዝ ውል መፈጸም አለባቸው።
  5. የጨረታው አሸናፊ ላልሆኑ ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተሰጠው በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል።
  6. ጨረታው ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ይዘጋል።
  7. ጨረታው ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
  8. ከጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
  9. ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በተመለከተ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ሃያ ሁለት መክሊት ህንፃ 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10-01

ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልገዎ በስልክ ቁጥሮች 0116-672342 ማነጋገር ይችላሉ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

 

Save Tender