የአፋር መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በመንገድ ፈንድ በጀት ለሚያካሄደው የተለያዩ መንገድ ጥገና ሥራዎች ላይ የሚሰማሩ iኛ ከ16 ሜትር ኪዩብ በላይየመጫን አቅም ያለው ግልባጭ መኪና፣ 2ኛ ከ17,000 ሊትር በላይ የሚጭን የነዳጅ ቦቲ፣ 3ኛ ከ20,000 ሊትር በላይ የሚጭን የውሃ ቦቲ ፣ 4ኛ 8 ሰው የመጫን አቅም ያለው ሰርቪስ መኪና፣ አይሱዚ መኪና፣ የፈረስ ጉልበቱ ከ1300hp የሆነ 1 D8R ዶዘር፣ እና የፈረስ ጉልበቱ ከ305 በለይ የሆነ ሎደር ማሽን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራይት ይፈልጋል።
የአፋር መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- አፋ/መን/ልማ/ትራ/ቢሮ 03/2018
የአፋር መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በመንገድ ፈንድ በጀት ለሚያካሄደው የተለያዩ መንገድ ጥገና ሥራዎች ላይ የሚሰማሩ 1ኛ ከ16 ሜትር ኪዩብ በላይየመጫን አቅም ያለው ግልባጭ መኪና፣ 2ኛ ከ17,000 ሊትር በላይ የሚጭን የነዳጅ ቦቲ፣ 3ኛ ከ20,000 ሊትር በላይ የሚጭን የውሃ ቦቲ ፣ 4ኛ 8 ሰው የመጫን አቅም ያለው ሰርቪስ መኪና፣ አይሱዚ መኪና፣ የፈረስ ጉልበቱ ከ1300hp የሆነ 1 D8R ዶዘር፣ እና የፈረስ ጉልበቱ ከ305 በለይ የሆነ ሎደር ማሽን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራይት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፦
ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1,000.00 በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ሠመራ በሚገኘው በዋና መ/ቤታችን ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃዳቸውን፣ የቫት ተመዘጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት፣ የግብርከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፊኬት እና የመንግስት መ/ቤቶች በሚፈጽሙት ግዥ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝጋባ ምስከር ወረቀት አብሮ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሽግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው። ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሠነዳቸውን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን አፋር መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ሆኖ ወዲያውኑ ሳጥን ታሽጎ በሚቀጥለው 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ቢሮ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሠመራ፣ ስልክ ቁጥር ፡-033-6-66-00-79 ደውለው ይጠይቁ።
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ
