የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ የ2018 በጀት ዓመት ትጥቅ ከሚያቀርቡ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Dire Kenema Sport Club (የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨ/ማ/ቁ/ድሬ ከተማ 001/18
የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ የ2018 በጀት ዓመት ትጥቅ ከሚያቀርቡ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- በሎት 1/ የወንድና የሴት እግር ኳስ ትጥቅ፣
- በሎት 2/ ለብስክሌት ቡድን ትጥቅ እና መለዋወጫ ዕቃ
- በሎት 3/ ለቦክስ ቡድን ትጥቅ፣
- በዘርፉ የተሠማሩ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በዘርፉ የአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝገቡ እና የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ጨረታ አግባብነት ያለው የተሟላ ማስረጃና ሠነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ከመስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም የጨረታ ሠነዱን ከድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ ሂሣብ ክፍል በአካል ወይም በወኪሎቻቸው በኩል ቀርበው በመስጠት አስፈላጊውን ዋጋ በግልጽ ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዋናውና ኮፒውን በአግባብ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 9፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታ መክፈቻ ቀን የተወዳደራችሁበትን የትጥቅ አይነት ሳምኘል ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በክለቡ ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር፡- 09-63-69-14-11 ወይም 09-21-16-05-10/09-15-76-42-84 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ
