Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት አማካኝነት በ2018 በጀት አመት በመደበኛ በጀት የሁሉም ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የእስቴሽነሪ እቃዎች፣ የቋሚ አላቂ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች ደንብ ልብስ የስፖርት ባለሙያዎች ደንብ ልብስ፣ የመኪና ጎማዎች የመኪና እስፔር ፖርቶች እቃዎች/፤ የሞተር ዘይቶች እና ሲሚንቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የአገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት አማካኝነት በ2018 በጀት አመት በመደበኛ በጀት የሁሉም ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የእስቴሽነሪ እቃዎች፣ የቋሚ አላቂ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የስፖርት ባለሙያዎች ደንብ ልብስ፣ የመኪና ጎማዎች የመኪና እስፔር ፖርቶች እቃዎች/፤ የሞተር ዘይቶች እና ሲሚንቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው።
  3. ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት ነገርግን የኮምፒዩተር እና ተዛማጅ እቃዎች አቅራቢ የብር መጠኑ ከ200,000 በታች ቢሆንም የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡
  4. ለመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ የሚችል ።
  5. ተጫራቾች ጨረታው ላይ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን እና ሌላም መረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በሁለት ኦርጅናል እና ኮፒ ብለው ማቅረብ አለባቸው።
  6. የሁሉንም እቃዎች ዝርዝር እስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኝት ይችላሉ፡፡
  7. መ/ቤቱ ካስቀመጠው ውጭ በራሱ ጊዜ እስፒስፊኬሽን የመጨመርና የመቀነሰ ወይም ያስቀመጠ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በዝ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት ጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እና በ16ኛው ቀን 2፡30-6:30 በተዘጋጀው ሳጥን በማስገባት በዚያው ቀን 8፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በዝ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግልፅ ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /በሰ.ፒ.ኦ/ ማስያዝ አለበት፡፡
  10. ተጫራቾች ከሚወዳደሩበት ሰነዱ ላይ ከእንዱ ዋጋው እና ጠቅላላ ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ ያደረገ ከጨረታው ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  11. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ የአንድ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ የሚለውን በጥንቃቄ ለያይተው መሙላት አለባቸው፡፡ ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊ ከሆኑ የጨረታውን ውል ማስከበሪያ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ትእዛዝ /ሰ.ፒ.ኦ/ በማስያዝ አሸናፊ መሆናቸውን ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  12. መ/ቤቱ በጨረታው ዙሪያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. የደንብ ልብስ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቶች ተቋሙ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት መሆኑ መታወቅ አለበት።
  14. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የመንግስት ስራ ዝግ ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀንና ሰዓት በተመሳሳይ ጊዜ ይከፈታል፡፡
  15. ማንኛውም ተጫራች ከኦርጅናል ሰነዱ ላይ የንግድ ፍቃዱን ኮፒ አድርጎ ፖስታው ላይ የማያስገባ ወይም ኮፒ አድርጎ ፖስታው ላይ ሳያስገባ ውጭ ላይ የተወ ከውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን ይታወቅ፡፡
  16. የጨረታ አሸናፊው አካል ውል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ቀጥታ በአስቸኳይ በውሉ መሰረት ንብረቱን ዝ/ወ/በሚገኘው ሴ/መ/ቤቶች ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት
  17. ይህ ውድድር ለ 1/አንድ/ አመት ሙሉ ስለሆነ ከላይ የተዘረዘሩት እቃዎች በአመቱ ውስጥ ሲያስፈልግ የሚያቀርብ መሆኑን ይታወቅ ።
  18. ለበለጠ መረጃ 0334620050/53/49 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል። ጽ/ቤቱ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት

Save Tender