Tender Detail

Tender Details

  • Company Awash Melkassa Chemical Factory (የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ)
  • Address ከአዳማ ከተማ 15ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ዋናው መ/ቤት ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022 220 266
  • Websitehttps://cicamcf.com.et/
  • Deadline14 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ ከ2% ያላነሰ
  • opening date2025-10-14 00:00:00
  • Categories Cctv Camera , System Supply And Installation

በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ በፋብሪካው በተለያዩ ቦታዎች ብዛታቸው 15 /አስራ አምስት/ የሚሆኑ CCTV Camera ለማስገጠም በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራ ይፈልጋል።

Awash Melkassa Chemical Factory (የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኬኢኮአመኬፋ 001/2018

 

በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ በፋብሪካው በተለያዩ ቦታዎች ብዛታቸው 15 /አስራ አምስት/ የሚሆኑ CCTV Camera ለማስገጠም በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራ ይፈልጋል።

ስለሆነም፡-

  1. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
  2. የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀትን ታክስ ክሊራንስ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገቡን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የስራ ቀናት አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንፃ ውስጥ ከአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ ከ2% ያላነሰ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ቼክ ወይም በባንኮች የተረጋጋጠ ጋራንቲ ደብዳቤ ከ90 ቀን ያላነሰ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ቴክኒካል አፈርና ፋይናንሺያል ኦፈር ኦሪጅናልና ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ ታሽገው ቴክኒካል ኦፈር፣ ፋይናንሺያል ኦፈር ተብሎ ተፅፎበት እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 በፊት ከአዳማ ከተማ 15ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ ቴክኒካል ኦፈሩ ብቻ በዕለቱ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ዋናው መ/ቤት ይከፈታል።
  7. ፋይናንሽያል አፈሩ ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ዋናው መ/ቤት ይከፈታል።
  8. ድርጅቱ/ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ፡- ስልከ ቁጥር 022 225 0266/022 225 0750

ሞባይል 0920935336

 

አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ

 

Save Tender