Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline13 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityበየ ሎቱ ይለያያል
  • opening date2025-10-13 00:00:00
  • Categories Office Supplies And Services , Ict And Telecom Service

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች እና የአይ ሲ.ቲ መለዋወጫ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)


                                                 የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 

                                                    ቁጥር 003/2018 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች እና የአይ ሲ.ቲ መለዋወጫ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

* በዘርፉ ስዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያስው 

* የንግድ ምዝገባ

* የግብር ከፋይ መስያ ቁጥር ሰርተፍኬት 

* የቫት ሰርተፍኬት

* በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ 

ሎት1. ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር፣ ሰርቨር እና ስዊች ግዥ)

ሎት2. አላቂ የአይሲቲ ዕቃዎች ከላይ በዝርዝር በቀረበው መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚሹ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የድጋፍ ደብዳቤ የጨረታ ሰነዱን በነጻ እንዲወስዱ ያስችላቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ስሎት1. 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ስሎት 2. 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.አ፣ ቢድቦንድ ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዶክመንት ዋና እና ቅጂ እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዋና እና ቅጂ በሚል በጉልህ በሚታይ መልኩ በመጻፍና የሚወዳደሩበትን ሎት በፖስታዎቹ ላይ በመግለጽ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን፤ የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒክ ዋና ስነድ ፖስታ ውስጥ ተያይዞ መገኘት አለበት። ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በጉልህ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቹ አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም። የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

* ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው 

አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

                                                                               የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

Save Tender