በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ/ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን የ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1. ተሸከርካሪ ጥገና፣ ሎት 2. ተሽከርካሪ ኢንሹራንስ፣ ሎት 3. ተሽከርካሪ ዲኮር፣ ሎት 4. ተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ሎት 5. ህትመት፣ ሎት 6. የፎቶ ኮፒ አገልግሎት፣ ሎት 7. የኮምፒውተርና ተዛማጅ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ሎት 8. የኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጥገና የእጅ ዋጋ፣ ሎት 9. የማሽነሪ መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 10. ተሽከርካሪ ዘይቶችና ቅባቶች አገልግሎት በኮንትራት ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ/ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ/ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን የ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1. ተሸከርካሪ ጥገና፣ ሎት 2. ተሽከርካሪ ኢንሹራንስ፣ ሎት 3. ተሽከርካሪ ዲኮር፣ ሎት 4. ተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ሎት 5. ህትመት፣ ሎት 6. የፎቶ ኮፒ አገልግሎት፣ ሎት 7. የኮምፒውተርና ተዛማጅ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ሎት 8. የኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጥገና የእጅ ዋጋ፣ ሎት 9. የማሽነሪ መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 10. ተሽከርካሪ ዘይቶችና ቅባቶች አገልግሎት በኮንትራት ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘርፋ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN /ቲን/ ነምበር ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተሽከርካሪ ጥገና ላይ የሚሳተፍ በዘርፉ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ያላቸው ሆኖ ደረጃ 2 ወይም ደረጃ 3 የሚያሟሉ መሆኑን የሚገልጽ ሰርተፍኬት አገልግሎት ሰጭ የጥገና ተቋማት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በተጫራቾች የሚቀርበው የመወዳደሪያ ዋጋ ለ40 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡
- የሚገዙት ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በምስ/ጐ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ በተከፈተው የዓባይ ባንክ አካውንት ቁጥር 2052117320503019 ወይም ለምስ/ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በተከፈተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000335896158 በመክፈል ከግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት 1. ተሽከርካሪ ጥገና 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ ሎት 2. ተሽከርካሪ ኢንሹራንስ /50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ሎት)፣ ሎት 3. ተሽከርካሪ ዲኮር /10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ ሎት 4. ተሽከርካሪ መለዋወጫ /50,000/ ሃምሳ ሺህ ብር/፣ ሎት 5. ህትመት 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ ሎት 6. የፎቶ ኮፒ አገልግሎት /1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/፣ ሎት 7, የኮምፒውተርና ተዛማጅ መለዋወጫ ዕቃዎች 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/፣ ሎት 8. የኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጥገና የእጅ ዋጋ 1,000,00 /አንድ ሺህ ብር/፣ ሎት 9. የማሽነሪ መለዋወጫ እቃዎች 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ሎት 10. ተሽከርካሪ ዘይቶችና ቅባቶች 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገንዘብ መምሪያ በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁ. 01 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ መግዛትና የመወዳደሪያ ሃሳብ ሞልቶ እስከ 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም የጨረታው መክፈቻ ቀን የበዓላት ቀን ወይም የካላንደር ዝግ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታው መክፈቻ ወቅት አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም ከሆነም ፓራፍ መደረግ አለበት፣ ኮሬክሽን ፍሉድ መጠቀም ከጨረታ ውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች መ/ቤቱ ካዘጋጀው የሥራ ዝርዝር ስፔስፊኬሽን/ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን ሎቶችን ማለትም ከሎት-4፣ ከሎት-7 እና ከሎት-9 በስተቀር ሌሎች ሎቶችን በደ/ማርቆስ ከተማ ላይ አገልግሎቱን መስጠት የሚችል።
- አሸናፊ የሚለየው በሎት ጥቅል ድምር ውጤት ዝቅተኛ ዋጋ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ የጨረታ ሰነድ ዝርዝር ላይ ዋጋ መሙላት አለበት፡፡ የጨረታ ሰነድ ዝርዝር ላይ ዋጋ መሉ ለሙሉ አለመሙላት ከጨረታ ውጪ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ወይም ውል የያዙባቸውን እቃዎች/አገልግሎቶች በምስ/ጎ/ዞን መምሪያዎች ባሉ የፑል ንብረት ክፍሎች ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፣
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ 5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ምስ/ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ምስ/ጐጃም ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ሕንፃ ግራውንድ ቢሮ ቁጥር- 01 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 05877716817 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡
በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ/ጎ/ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብ/አስ/ቡድን
