በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘአ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለአብቹና ኘአ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት በወረዳው በሚገኙ በተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ በ2018 በጀት ዓመት በኮዋሽ ፕሮግራም በጀት 5(አምስት)ጥልቀቱ 50 (ሃምሳ )ሜትር የሆነ የአጭር ጉድጓድ (shallow well) አወዳድሮ ማስቆፈር ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ፕአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአጭር ጉድጓድ (shallow well) ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘአ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለአብቹና ኘአ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት በወረዳው በሚገኙ በተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ በ2018 በጀት ዓመት በኮዋሽ ፕሮግራም በጀት 5(አምስት)ጥልቀቱ 50 (ሃምሳ )ሜትር የሆነ የአጭር ጉድጓድ (shallow well) አወዳድሮ ማስቆፈር ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት:-
1ኛ ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊና የዘመኑ የታደሰ የቁፋሮ (drilling) የፒ.ኤል.ሲ. (PLC) የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጨረታዉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
2ኛ የግብር ከፋይ መለያቁጥር ቲን ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
3ኛ ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር የያዘው የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሥራውን ዝርዝር (specification) የማይመለስ ሁለት 200 ብር በመክፈል ዘወትርበሥራ ሰአት በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
4ኛ/ ተጫራቾች በሰነድ የሞሉትን ዋጋ በኦርጅናልና ኮፒ ብቻ ለብቻ በማድረግ በዋናው ፖስታ በማሸግ በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የፕሮጀከቱን ባለቤት ስም፣ የፕሮጀከቱ አይነት፣ የፕሮጀከቱን ባለቤት አድራሻ፡ የተጫራቹ ድርጅት ስም እና የድርጅቱ ተወካይ አድራሻ በመፃፍ በእያንዳንዱ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ አለበት፡፡
5ኛ/ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 21 (ሃያአንድ ) ተከታታይ የሥራ ቀናት በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
6ኛ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳሺ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7ኛ ጨረታው የሚከፈተው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት በሃያ አንደኛው ቀን ሆኖ በዚያው ቀን በ6፡00 ሰአት ታሽጎ በ8፡30 ሰአት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
8ኛ የዘርፉን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
9ኛ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 01 16210270 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብቹና ኘአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
መንዲዳ
ማሳሰቢያ፡- መሥሪያቤቱ የፕሮጀከቱን ብዛት በ25% (ሃያአምስት ፐርሰንት) መጨመር ወይም መቀነስም ይችላል::
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘስ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
