በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ለ2ኛ (ለሁለተኛ) ጊዜ በ2018 የበጀት አመት ለገላን ክ/ከተማ አገልግሎት የሚውሉ ኮድ -3 አውቶሞቢልና ኮድ-3 ፒካፕ (pik-up) መኪና በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
ለ2ኛ (ሁለተኛ) ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ለ2ኛ (ለሁለተኛ) ጊዜ በ2018 የበጀት አመት ለገላን ክ/ከተማ አገልግሎት የሚውሉ ኮድ -3 አውቶሞቢልና ኮድ-3 ፒካፕ (pik-up) መኪና በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ መረጃዎች በማቅረብ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፍ ይጋብዛል፡፡
-
- በዘረፉ ህጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
- አቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ተጋቢ የሆነ።
- የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት እና በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 2000.00 (ሁለት ሺ) ብር በገላን ክ/ከተማ ገቢዎች ባለስልጣ ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ/ በፖስታ/በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ተዘግቶ ልክ በዚሁ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባችዋል።
- ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቻው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10 % በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተገለፀው መሰረት የተጫረቱበት ዕቃ ናሙና /Sample/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይችልም፡፡
- የመወዳደሪያ በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 4 45 01 82 በመደወል እና በአካል ተገኝቶ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ:- በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ገላን
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት
