Tender Detail

Tender Details

  • Company የኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን
  • Address ቂርቆስ ክ/ከተማ ከግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114-66-54-59
  • Website
  • Deadline06 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityከጠቅላላ ዋጋ 1%
  • opening date2025-10-06 00:00:00
  • Categories Building Materials , Metals And Metal Working , Construction Materials And Raw Materials

የኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በስሩ ለሚገኙ ማረሚያ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት ለጥገና እና ለታራሚዎች መኝታ አገልግሎት የሚውል ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መጠን ያላቸው የዓርማታ ብረቶች በግልፅ ጨረታ አውዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ኦማቤኮ 2018/1

 

የኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በስሩ ለሚገኙ ማረሚያ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት ለጥገና እና ለታራሚዎች መኝታ አገልግሎት የሚውል፡-

ሀ. ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መጠን ያላቸው የዓርማታ ብረቶች በግልፅ ጨረታ አውዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ወይንም አቅራቢዎች እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

  1. የታደሰ እና በግዥው ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው።
  2. በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ህጋዊ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና የከፈሉበትን ማስረጃ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተመዘገቡ እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ቢጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) አ/አበባ ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው የኮሚሽኑ ጽ/ቤት የግዥ እቅድ ዝግጅት እና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የቴክኒክ እና ፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦሪጂናሉን እና ኮፒውን በተለያዩ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀን በአየር ላይ ውሎ በአስራ ስድስተኛው የሥራ ቀን ከቀኑ በ6፡30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8:00 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ አስራ ስድስተኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ በተወዳደሩበት ዘርፍ ከጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ ከፍያ ቼክ (CPO) ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የሚያቀርቡት ሠነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. ለተጨማሪ ማብራሪያ 0114-66-54-59 ወይም 0913-063-056 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  10. ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን

ኣድራሻ፡- ቂርቆስ ክ/ከተማ ከግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት

 

የኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን

 

Save Tender