Tender Detail

Tender Details


የዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡ/ ሥራ ሂደት በሆስፒታሉ ዉስጥ ያሉ ጠቅላላ የፅዳት ስራ ፣ የጥበቃ ስራ የህሙማን በሰሉ ምግብ አቅርቦት ፣ የመኪና ጥገና ስራ፣ የኦክስጅን ሙሌት እና አክስጅን ሲሊንደር ደርሶ መልስ ጭነት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዓለም ከተማ የእናት ጠቅላላ ሆስፒታል


                                                                     ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 የዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡ/ ሥራ ሂደት በሆስፒታሉ ዉስጥ ያሉ ጠቅላላ የፅዳት ስራ ፣ የጥበቃ ስራ የህሙማን በሰሉ ምግብ አቅርቦት ፣ የመኪና ጥገና ስራ፣ የኦክስጅን ሙሌት እና አክስጅን ሲሊንደር ደርሶ መልስ ጭነት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉና ማቅረብ የሚችሉ 

  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ 

  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲንነበር/ መዝጋቢና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል 

  4. ተጫራቾች በሚጫረቱበት መስክ አግባብ ያለው ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

  5. የግዥዉ መጠን ከ200,000 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ መሆኑ ሲገመት ተጫራቾች /የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡ 

  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍና የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከላይ በተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውንና ኦርጅናል ሰነዶቻቸውን ማቅረብና ማመሳከር ይኖርባቸዋል፡፡ 

  7. የጨረታ ሰነዱ በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝ ያለበት ከሆነና ለመለየት አሻሚ ከሆነ ዋጋ አይኖረውም፡ 

  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ለመግዛት የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል ዓለም ከተማ እናት ጠቅላላ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር - 03 በመምጣት መውሰድ ይቻላል፡፡ 

  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ የአገልግሎቱ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ 

  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋናና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ በı ወጥ ወይም በ2 ወጥ ፖስታ በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 

  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም/በ16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 

  12. ተጫራቾች ለአገልግሎቱ ዓይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ መሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት አገልግሎት አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችሉም ማለት በሎት በሚወዳደርበት ስዓት ያልሞሉት ዋጋ ካለ ውድቅ ይሆናል፡፡ 

  13. የፅዳት ስራው በሬሾው መሰረት ማፅዳት የሚችል፤ የመኪና ጥገና አገልግሎት መስጠት የሚቻለው በአካባቢው ላይ ቅርንጫፍ ያለው መሆን አለበት እንዲሁም የምግብ የማብሰያ እቃ ያላቸው መሆን አለበት 

  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዓ/ከ/አ/ጠ/ሆ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር -03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር oilm320741 ወይም በስልክ ቁጥር 0913089057 በመደወል ማግኘት ይችላል፡፡ 

  16. የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ማሳሰቢያ፡- ከላይ የተዘረዘሩት የተጫራቾች መመሪያ ከአጠቃላይ የተጫራቾች ዝርዝር መመሪያዎች በከፊል ተወሰዱ መሆናቸው ይታወቅ፡፡ 

                                                                በዓለም ከተማ የእናት ጠቅላላ ሆስፒታል

Save Tender