ኩባንያችን ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ መናኸሪያ አካባቢ በሚገኘው በዋናው መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ የስራ ቦታውን አጠቃቀም እና ተግባራዊነት ደረጃ /Strategic Site Plan and Land Use Pre-feasibility Study/ ለማሰራት የተዘጋጀው /TOR/ መነሻ ሃሳብ መሰረት በማድረግ ጥናታቸውን በማከናወን የሚያቀርቡ በዚህ መስክ የተሰማሩ አማካሪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
Tsehay Industry S.C. Kaliti Metal Products Factory (ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ)
የፕሮጀክት ቦታ አጠቃቀም እና ትግበራ ጥናት ሥራ አገልግሎት ግዥ ግልፅ
ጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ መናኸሪያ አካባቢ በሚገኘው በዋናው መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ የስራ ቦታውን አጠቃቀም እና ተግባራዊነት ደረጃ /Strategic Site Plan and Land Use Pre-feasibility Study/ ለማሰራት የተዘጋጀው /TOR/ መነሻ ሃሳብ መሰረት በማድረግ ጥናታቸውን በማከናወን የሚያቀርቡ በዚህ መስክ የተሰማሩ አማካሪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት፡-
- በሥራ መስክ ለመሰማራት በዘርፉ ካሉ የመንግስት አካላት የተሰጠ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ማስረጃ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የድርጅት አቋም መግለጫ (Company Profile) እና መንደርደሪያ ሀሳብ (Proposal) ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያለው ተጫራች ለዚሁ የተዘጋጀውን ቢጋር (TOR) እና የጨረታ መግለጫ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ የግዢ ዋና ክፍል በመውሰድ በጨረታው የሚወዳደሩበት የፕሮጀክቱን የጥናት፣ የዲዛይን ስፔሲፊኬሽን ሥራ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሠነዶቻችውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት በፊት ዘወትር በስራ ሰዓት ከታች በተገለፀው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- በጨረታው የሚቀርበው የቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነድ ለየብቻ በስም በታሸገ ፖስታ ሆኖ በፋይናንሺያል ሰነድ ውስጥ የሚቀርበው የአገልግሎት ዋጋ ለአዋጭነትና እና ዲዛይን ስራው ለየብቻ መሆን ይኖርበታል።
- ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ ብር 20,000 - (ሃያ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና መቅረብ ይኖርበታል።
- ጨረታው መስከረም 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 4 34 01 10 ወደም 011 4 34 40 06 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- ከቃሊቲ መናኸሪያ ዝቅ ብሎ ቶታል ማደያ ፊት ለፊት ባለው አስፋልት 700 ሜትር ገባ ብሎ ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ
ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ
