በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ለፒቪሲ ምርት ማምረቻ የሚሆን ፒቪሲ ሬዝን ዕቃ 100,000 ኪ.ግ እና ስታብላይዘር (Stabilizer) መቀላቀያ ጥሬ ዕቃ ብዛት 4,500 ኪ.ግ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ለፒቪሲ ምርት ማምረቻ የሚሆን ፒቪሲ ሬዝን ዕቃ 100,000 ኪ.ግ እና ስታብላይዘር (Stabilizer) መቀላቀያ ጥሬ ዕቃ ብዛት 4,500 ኪ.ግ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ፡-
- በኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾችን መመሪያ እና የዕቃዎችን ዓይነትና መጠን የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- በዋጋ ማቅረቢያው ቅፅ ላይ ተጫራቹ የዕቃው ዋጋ በሚለው ዓምድ ስር የሚሸጡበትን የነጠላ ዋጋ በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ የኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቹ የዕቃዎችን የተናጠል ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ትከክለኛ የተጫራች ስምና አድራሻ በታሸገው ኢንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነድ ላይ መገለጽ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የዕቃዎችን ለተቀመጠው የነጠላ ዋጋ ድምር የጨረታ መነሻ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታ ሣጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ጠዋት በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።
- ተጫራቾች የጨረታውን ውጤት በኢንዱስትሪው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ የሥራ ቀኖች ውስጥ በጽሑፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥራችን 011 66 70 485 / 011 85 92 286 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ በየገፁ ስምና ፊርማ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የቫት ሠርተፍኬት፣ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ ሠርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፡- በመናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ከአምቼ ዝቅ ብሎ ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ
አዲስ አበባ
