Tender Detail

Tender Details


ኮርፖሬሽናችን ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጸውን GPS ግዥ አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Hibir Construction Corporation (ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)


 

የGPS ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኀብኮን 03/2018 (በድጋሚ የወጣ)

 

ኮርፖሬሽናችን ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጸውን GPS ግዥ አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የሚገዛው ዕቃ አይነት

መለኪያ

ብዛት

GPS የሚፈለግበት ፕሮጀክት

ምርመራ

1

GPS

በቁጥር

3

ለተለያዩ ፕሮጀክቶች

 

 

ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም አቅራቢ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላል።

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የተ.እ ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ቁጥር እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣታቸው የሚገልጽ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል በኮርፖሬሽናችን ስም የተሰራ የባንክ ጋራንቲ የተ.እ. ታክስን ጨምሮ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ አለባቸው።
  3. ኮርፖሬሽናችን አሸናፊውን ተጫራች ድርጅት በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን የGPS መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 50% ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል።
  4. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዥ ለተገለጸው የGPS አቅርቦት ቴክኒካል አሪጅናል እና ኮፒ ለብቻ እንዲሁም የዋጋ መሙያ ፋይናንሻል ሰነድ ቅጅ እና ዋና ለየብቻ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያን በፖስታ በማሸግ ማያያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  6. ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 9:10 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከኮርፖሬሽናችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-220-45-79 መደወል ይችላሉ፡፡

 

ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን

 

Save Tender