Tender Detail

Tender Details


በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በስሩ ለሚገኙ ለሁሉም ፋብሪካዎች የኢአርፒ ትግበራ ለማስጀመር የሚውሉ ለኔትወርክ ዲቫይስ እና ኦፕሬቲንግ ሶፍትዌር ግዥ በብሔራዊ ግልጽ የጨረታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በስሩ ለሚገኙ ለሁሉም ፋብሪካዎች የኢአርፒ ትግበራ ለማስጀመር የሚውሉ ለኔትወርክ ዲቫይስ እና ኦፕሬቲንግ ሶፍትዌር ግዥ በብሔራዊ ግልጽ የጨረታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 (አንድ) ለኔትወርክ ዲቫይስ እና አፕሬቲንግ ሶፍትዌር ግዥ

ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ግዥ

ስለሆንም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ተጋብዟችኋል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) ማስረጃ ማቅረብ አለበት
  4. ተጫራቾች በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስም ለሎት 1 (አንድ) ለኢአርፒ የሚውል ለኔትወርክ ዲቫይስ እና ኦፕሬቲንግ ሶፍትዌር ግዥ ብር 50,000 (ሀምሳ ሺ ብር) በብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ (CPO)፣ ቼክ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለየብቻው ከሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትከክል መሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለበት፡፡
  6. ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት
  7. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢክፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ አንደኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ የሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ 2ኛ ፎቅ ላይ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  9. ተጫራቶች ለጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዱን ለየብቻ ለይቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት አየር ላይውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይዘጋል፡፡ በዚሁ ዕለትም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3ኛ ፎቅ ላይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  11. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
  12. ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 60 (ስልሳ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾችም ይህንኑ አውቀው ስለመቀበላቸው በሰነዳቸው ላይ ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
  13. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም፡፡ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ለቡ መብራት ኃይል ከጀነራል መርከንታይል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ፡- በስልከ ቁጥራችን +251 912450566 +251 910162733 +251 921899555 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ

 

Save Tender