Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 11 ፊሊጶስ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 11 ፊሊጶስ ጤና ጣቢያ


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 11 ፊሊጶስ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም፡-

ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያ ግዥ

ሎት 2. የፅዳት እቃዎች ግዥ

ሎት 3. የደንብ ልብስ ግዥ

ሎት 4 የቋሚ እቃዎች ግዥ

ሎት 5. የህንፃ ቁሳቁስ ግዥ

ሎት 6. የህትመት ግዥ

ሎት 7. የሚንስትርሚንግ እቃዎች ግዥ

ሎት 8. የመድሀኒት፣ የሪኤጀንት እና የህክምና መሳሪያ ግዥ

ሎት 9. የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ

ከላይ በሎት የተዘረዘሩት እቃዎች ድርጅታችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡ፣ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  2. አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በአዋጁ መሠረት የተቋቋሙ አምራች በሆኑበት ዘርፍ ብቻ ወይም በሚያመርቱት እቃ ብቻ ካደራጃቸዉ አካል በሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ተቋማቱ አምራች ባልሆኑበት ዘርፍ በዋስትና ደብዳቤ አናስተናግድም።
  3. መድሀኒት እና ሪኤጀንት ግዥ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን /EFDA የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የሚፈለገውን ሁሉንም በተጫራቾች እንዲሞሉ የሚጠየቁትን ክፍል 4 እና ሌሎችም በተጫራቾች መሞላት ያለባቸውን ክፍሎች ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል በተጫራች የሚሞሉ ክፍሎችን ሞልቶ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል።
  5. መደበኛው የጨረታ ሰነድ ሳይገነጠል በሙሉ ተመላሽ መሆን ይኖርበታል /ሙሉ ሰነድ ተመላሽ ያላደረገ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል።
  6. ተጫራቾች ከጨረታ መዝጊያ ሶስት (3) ቀናት በፊት ቀደም ብለው ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ እስከ መስሪያ ቤቱ ድረስ ለማምጣት ቀላል እና ለማንቀሳቀስ ከባድ ያልሆኑ እቃዎች በሙሉ በአካል መቅረብ ይኖርባቸዋል/ ለማንቀሳቀስ ከባድ ያልሆኑ እቃዎች የፎቶ ሳምፕል / ናሙና አንቀበልም።
  7. በፎቶ የሚቀርቡ ናሙናዎች ከለር ፕሪንት ሆነው ስለ እቃው ግልፅ የሆነ የፅሁፍ ማብራሪያ ሊኖረው ይገባል።
  8. መ/ቤቱ በጨረታ ከቀረበው የእቃ ብዛት እስከ 20% መቀነስም ሆነ መጨመር ይችላል።
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ለጨረታ ማስከበሪያ የባንክ CPO, ሎት1= 5000 (አምስት ሺህ ብር)፣ ሎት. 2 = 6000 (ስድስት ሺህ ብር)፣ ሎት.3 = 10,000 (አስር ሺህ ብር)፣ ሎት.4 = 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)፣ ሎት. 5 = 8,000 (ስምንት ሺህ ብር)፣ ሎት. 6 = 5,000 (አምስት ሺህ ብር)፣ ሎት.7= 4,000 (አራት ሺህ ብር)፣ ሎት.8 = 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)፣ ሎት. 9 = 3000 (ሶስት ሺህ ብር) ሲሆን ከዚህ ውጪ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት አይኖረውም።
  11. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ 4ኛ ፎቅ/ ግዥ ክፍል/ ቢሮ ቁጥር 68 መጥተው መግዛት ይችላሉ።
  12. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ አስር (10) ተከታታ የስራ ቀናት ተቆጥረው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጨረታ ኮሚቴ እና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ታሽጎ በዚያው እለት ወዲያውኑ 4፡30 ይከፈታል።
  13. በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ኦርደር ከተሰጠው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ውል ማስከበሪያ ሲፒኦ በማቅረብ ውል መግባት ይኖርበታል።
  14. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ መደበኛ የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት, ፋይናንሻል ኦርጂናል፣ ፋይናንሻል ኮፒ፣ ቴክኒካል ኦርጂናል፣ ቴክኒካል ኮፒ፣ ለየብቻ በካኪ ፖስታ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም አድርገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ፡- ከኮልፌ አጠና ተራ ወደ ሎሚ-ሜዳ በሚወስደው መንገድ/ ፊሊጶስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት እንገኛለን።

ስልክ:- 011-2-73-92-45

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 11 ፊሊጶስ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender

በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE
ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃ.የተ.የግ.ማ. በአዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳርና ጂማ በሚገኙ ፕሮጀክቶቹ ላይ ለሲቪል፣ ኤሌክትሪክ፣ ሜካኒካል፣ ሳኒተሪ፣ የውስ...

READ MORE