Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት
  • Address ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462125584
  • Website
  • Deadline19 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2025-08-19 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያሠራ ላቀደው የሕንጻ እድሳት ሥራ ለማሠራት ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2018 በጀት ዓመት በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያሠራ ላቀደው የሕንጻ እድሳት ሥራ ለማሠራት ሕጋዊ ተጫራችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

በዚሁ መሠረት -

  1. ደረጃቸው GC-6/BC-6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተቋራጮች 2017 . ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ወይም ከሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።
  2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው
  3. በሲዳማ ክልል ውስጥ ሶስት (3) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀቶችን ውል ገብተው ግንባታ እያከናውኑ ያሉ እና ያላስረከቡ ሥራ ተቋራጮች ይህን የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፣
  4. በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ሕጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሠሪ መሥሪያ ቤት ወይም ማካሪ መሥሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  5. የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦርጅናል) ሲጠየቁ ቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳ ክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 80,000.00 (ሰማንያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና (BANK GAURANTEE) ወይም ፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
  7. የስራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፈቃዳቸውን እና ተዕታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬትና ታክስ ሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ 12 (አሥራ ሁለት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብ/ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታውን ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
  9. የጨረታው ሰነድ በተጫራ መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security) ፋይናንሻል እንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ (ኮፒ) እንዲሁም ኒካል ንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ (ኮፒ) ሰነዶችን በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ ንድ ትልቅ ፓስታ ውስጥ ተከትተው በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 13ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 እስከ 6:00 ሰዓት የሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሽግ አለበት፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ከቀኑ 600 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት ያግደውም፡፡
  10. አሠሪው መሥሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ሙበት አለው
  11. አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል።
  12. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡

በለጠ መረጃ ስልክ- 0462125584 ይደውሉ፡፡

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት

 

Save Tender

Procurement Reference Number: GRRA/RCFSP/E308-ET/NCB/CON/2026/03

READ MORE
Procurement Reference Number: GRRA/RCFSP/E308-ET/NCB/Mai/2026/06

READ MORE
Procurement Reference Number: GRRA/RCFSP/E308-ET/NCB/CON/2026/04

READ MORE