Tender Detail

Tender Details


የመርቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶችና የቀበሌ አስተዳደሮች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 2. የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ ሎት 3 የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 4. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት5. ፈርኒቸር፣ ሎት6, የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።.

የመርቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የመርቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶችና የቀበሌ አስተዳደሮች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 2. የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ ሎት 3 የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 4. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት5. ፈርኒቸር፣ ሎት6, የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።.

በመሆኑም: -

  1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና በፌዴራል፤ በከልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ ለጽህፈት መሣሪያዎች እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) ፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸርእቃዎች፣ ለጽዳት እቃዎች እና ለደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 350.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ) በመርቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በሂሳብ ቁጥር1000075175648 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ ንብረት አስተዳደር መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመመላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ የስብሳባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒከስ እቃዎች፤ ለጽህፈት መሣሪያዎች እና ለመኪና ጎማዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ) ፤ ለደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20.000.00 (ሃያ ሺህ) እንዲሁም ለጽዳት እቃዎች እና ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንከ በከፍያ ማዘዣ(CPO) ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አቦምሳ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የዞኑ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
  7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁጥር 0913938455/0913395762 ይጠይቁ።

                    የመርቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender

በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት ለማሟያ የሚሆን በአንደኛ ዙር ያልተከናወኑ የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደ...

READ MORE