Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ ደ/ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን
  • Address ኮምቦልቻ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0335514657
  • Website
  • Deadline19 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityለሎት -1- 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለሎት-2- 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/፣ ለሎት-3- 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ ለሎት-4- 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለሎት-5- 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/
  • opening date2025-08-19 00:00:00
  • Categories Petroleum Products Fuel, Diesel , Oil And Lubricant , Veterinary Equipment And Supplies , Vehicle Battery , Vehicle tire , Vehicle Spare Parts

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ ቡድን ለቃሉ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት-1- የእንስሳት መድሃኒት ሎት -2- አላቂ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት-3- የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ ሎት-4- ልዩ ልዩ ዓመታዊ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት-5- የመኪና ቅባትና ዘይት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአብክመ ደ/ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን


 

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ ቡድን ለቃሉ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት-1- የእንስሳት መድሃኒት ሎት -2- አላቂ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት-3- የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ ሎት-4- ልዩ ልዩ ዓመታዊ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት-5- የመኪና ቅባትና ዘይት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. የጨረታ መለያ ቁጥር-ቃ/ወ/ግ/ጨ/001/2018
  2. ተጫራቶች ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ቲን ነምበር ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና መረጃ ኦርጂናል እና የማይመለስ ኮፒ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ ሲኖርበት የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  3. የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ ነው፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት 11፡00 ሰዓት ድረስ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.9 በመምጣት የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ፡፡
  5. ተጫራቾች ለሎት -1- 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለሎት-2- 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/፣ ለሎት-3- 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ ለሎት-4- 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለሎት-5- 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ በቢድ ቦንድ ከሆነ ከ60 ቀን ያነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋናና ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ አሽጎ ስምና አድራሻውን በመጻፍ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ በድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ፖስታውን ማስገባት የሚቻል ሲሆን በዚሁ እለት 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው እለት የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
  8. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  9. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በአሸነፈበት ዋጋ በፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል ለመውሰድ ፍቃደኛ የሆነ መሆን አለበት፡፡
  10. በሎት 4 ላይ የተገለጹትን እቃዎች የአንዱን ዋጋ በመሙላት አመታዊ የኮንትራት ውል የሚወሰድ ሲሆን በውሉ መሰረት እቃዎቹን ተቋማት በሚፈልጉት መጠን መሰረት በወረዳችን ንብረት ክፍል ድረስ ለማቅረብ ፍቃደኛ መሆን ሲኖርበት ሎት 1 ፣ ሎት 2 ፣ ሎት 3 እና ሎት 5 የተገለጹት እቃዎች በአንድ ጊዜ በጥቅል ንብረት ክፍል የሚገቡ መሆኑ መታወቅ አለበት።
  11. ውድድሩ የሚካሄደው በእያንዳንዱ ሎት ድምር ነው።
  12. ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ሲያጋጥም በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
  13. መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከአሸነፈው እቃ ወይም ገንዘብ መጠን ላይ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ተጫራቾች ክልሉ ላወጣቸው የግዥ አፈጻጸም መመሪያዎች ተገዥ መሆን ሲኖርባቸው ማሸነፉ ከተነገረ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  15. አሸናፊው ተወዳዳሪ ኦርጂናል እቃዎችን ማቅረቡ ግዴታ ሲሆን ተጫራቾች ሰነድ ሲገዙ ጽ/ቤታችን ለሎት 2፤3 እና 4 ለተገለጹት እቃዎች ያዘጋጃቸውን ናሙናዎች በማየት በናሙናው መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  17. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቃሉ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0335514657 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

በአብክመ ደ/ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን /ኮምቦልቻ/

 

Save Tender