ግዮን የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ የኃ/የተ/የግ/ ማህበር ለቢራ ካሳ ወንበርና ጠረጴዛ ማምረቻ የሚሆን ጥሬ እቃ HDPE, RECYCLE HDPE, PP RAFFIA, RECYCLE PP, DIFFERENT COLOR MASTERBACH/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግዮን የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ የኃ/የተ/የግ/ ማህበር
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/ግ/2025
ግዮን የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ የኃ/የተ/የግ/ ማህበር ለቢራ ካሳ ወንበርና ጠረጴዛ ማምረቻ የሚሆን ጥሬ እቃ HDPE, RECYCLE HDPE, PP RAFFIA, RECYCLE PP, DIFFERENT COLOR MASTERBACH/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ከመጫረቻ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር /ቲን/ እና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ከዋናው ጋር የተገናዘባ የምስክር ወረቀት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፤
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ በጥንታቄ በታሸገ ፖስታ ወይም በባህርዳር ከተማ አፄ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ ግዮን የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ወይም DHL በድርጅቱ አድራሻ መላክ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ክፍት ሆኖ በቀጣዩ ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ አጼ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ በሚገኘው ግዮን የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋበት ቀን ክብረ በዓል ከሆነ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዮን የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ ኃ/የተ/የግ ማህበር ባህር ዳር ከተማ አጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583210030 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱን አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር አምባሰል ህንጻ 1ኛ ፎቅ በቁጥር 107 ወይም ባህርዳር ግዮን የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ ኃ/የተ/የግ ማህበር ቢሮ ቁጥር 5 በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት ማግኘት ይችላሉ፡፡
ግዮን የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ የኃ/የተ/የግ/ ማህበር
