በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል የሰራተኞች የመኪና ሰርቪስ አገልግሎት፣ የኦክስጅን የመድሃኒት እና የመኪና ጭነት አገልግሎት ፣ የመድሃኒት ሰፕላይ እና ሪኤጀንት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል የሰራተኞች የመኪና ሰርቪስ አገልግሎት፣ የኦክስጅን የመድሃኒት እና የመኪና ጭነት አገልግሎት ፣ የመድሃኒት ሰፕላይ እና ሪኤጀንት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነበር ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር ያለው ጨረታው ለማሸነፍ የሠጠው አመታዊ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ በመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦርጅናሉንና ኮፒ በጥንቃቄ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ዝርዝር መግለጫ /እስቴስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ፡፡ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመያዝ በአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የተወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1% እና ካሸነፈ በኋላ ያሸነፈበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታል ገንዘብ ቤት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢሮ ግዥ ፋይናስ ቁጥር 44 የስራ ሂደት በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ 3፡30 ሰዓት ላይ ወዲያው ይታሸጋል፡፡ 4፡00 ሰዓት ላይ ወዲያው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር በሞባይል 0913005480 /0913034113 /0913023571 ቁጥር በመደወል መጠየቅ ይቻላል ፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ፀንቶ ለ 20 / ሃያ / ቀን ይቆያል፡፡
- የመክፈቻው ዕለት በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁትን ሁኔታዎች ቢኖሩ በግዥ መመሪያው ተግባር መሆን አለባቸው።
- ለወሰዱት የተጫራቾች መመሪያ ለእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታችሁን ማህተም ማድረግ እና አብረው ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- ግብር የከፈሉበት ክሪላንስ ከግቢዎች ፅ/ቤት አብረው ማስያዝ አለባቸው።
- ጨረታውን በጥቅል የምናወዳድር መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ በሆስፒታሉ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
