Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Railway Corporation (የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን)
  • Address ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከጉምሩክ ኮሚሽን ፊት ለፊት ባቡር መሻገሪያው ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0963-576235
  • Websitehttps://erc.gov.et/
  • Deadline28 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security50000.00
  • opening date2025-07-28 00:00:00
  • Categories

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ በሚገኘው በዋና መስራቤት ግቢ ውስጥ ለሚገኘው የ batching plant security camera /CCTV/ አቅርቦት ዝርጋታና ኮሚሽን ስራዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Railway Corporation (የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን)


 

የCCTV ካሜራ አቅርቦት፣ ዝርጋታና ኮሚሽን ስራዎች ግዥ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

(የግዥው መለያ ቁጥር-ERC/BDD/EP/B021/2025)

 

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ በሚገኘው በዋና መስራቤት ግቢ ውስጥ ለሚገኘው የ batching plant security camera /CCTV/ አቅርቦት ዝርጋታና ኮሚሽን ስራዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው!
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚቀርቡት ካሜራ እና ዝርጋታ ስራ በጨረታ ሰነዱ የተገለፁትን መስፈርቶች አሟልተዉ መቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 50,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ማቅረብ አለባቸዉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር-32 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ29/10/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 21/11/2017 ዓ.ም (ጨረታው እስከሚዘጋበት) በኮርፖሬሽኑ መ/ቤት በአካል በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያውን፣ ፋይናንሻልንና ቴክኒካል ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ በማድረግ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 21/11/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በ21/11/2017ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከሰአት በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር+251114702044- በስልክ ቁጥር 0114702058 ወይም 0114702051/0966800400 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

(አድራሻ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ፣ አዲስ አበባ (ሴራሊዮን መንገድ /መሿለኪያ) ፣ ስልክ

0114702058/0114702051/0966800400: ፋክስ +251114702044 ኢሜል -erailways@erc.gov.et, bethel_erc_eng_procur@erc.gov.et)

 

Save Tender